1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርዶጋን ድልና አንድምታው

ሰኞ፣ ግንቦት 21 2015

ላልፉት 20 አመታት ቱርክን የመሩት ሚስተር ኤርዶጋን፤ በአገራቸው በሰብዓዊ መብት ጥሰት፤ የኢኮኖሚ ችግርና ስልጣንን በማማክል ከሚከሷቸው ተቃዋሚዎቻቸው ባላነሰ፤ የኔቶና የአውሮጳ ህብረት ወዳጆቻቸውም ዛሬም በመንበረ ስልጣናቸው ባያዩዋቸው እንደሚመርጡ የምዕራባውያን ጋዜጦችና መገናኛ ብዙሀን ሳይሸሽጉ ሲዘግቡ ነበር የቆዩት።

https://p.dw.com/p/4RwOZ
Türkei Präsidentschaftswahl Erdogans Anhänger
ምስል Emrah Gurel/AP Photo/picture alliance

የኤርዶጋን ድልና አንድምታው


በሁሉም የአለማችን ከፍሎች በተለይም በአውሮጳ ከፍተኛ ትኩረትን  ስቦ የነበረው የቱርክ ምርጫ ዛሬም ፕሬዝደንት ኤርዶጋንን አሸናፊ  አድርጎ ተጠናቋል። በጠቅላይ ሚኒስትርነትና ፕረዝዳትነት ላልፉት 20 አመታት ቱርክን የመሩት ሚስተር ኤርዶጋን፤ በአገራቸው በሰባዊ መብት ጥሰት፤ የኢኮኖሚ ችግርና  ስልጣንን በማማክል ከሚከሷቸው ተቃዋሚዎችቸው ባላነሰ፤ የኔቶና የውሮፓ ህብረት ወዳጆቻቸውም ዛሬም በመንበረ ስልጣናቸው ባያዩዋቸው እንደሚመርጡ የምራባውያን ጋዜጦችና መገናኛ ብዙሀን ሳይሸሽጉ ሲዘግቡ ነበር የቆዩት። ሆኖም ግን ባለፈው ግንቦት 6 ቀን የተክሂደው የመጅመሪያ ምርጫ የፕሬዝዳንቱን ፓርቲ አብልጫ የፓርላማ ወንበር ካስገኘና እሳቸውም በ5 ከመቶ ልዩነት ተፎካካሪያቸውን በመምራት ለዳግም የመለያ ምርጭ ማለፋቸው የትናንትናውን ድል  በቅድሚያ ያመላከት እንድነበር ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት።
 
በዘመናዊቷ ቱርክ ታሪክ ውስጥ፣ ቱርክ፤  ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት እንድታስመዘግብና በአካባቢያዊና አለማቀፍዊ ፖለቲካም አይነተኛ ሚና እንዲኖራት እንዳስቻሉ የሚነገርላቸው ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን፤ ዘንዶሮ ስልጣናቸውን ያጧት ይሆናል ተብሎ የተገመተው፤ ኢኮኖሚው በማሽቆልቆሉ፤ በቅርቡ ተከስቶ በነበረው የርዕደ መሬት አደጋ የመንግስቸው ምላሺ አጥጋቢ ስላልነብር፤ በዴሞክራሲና የፕሬስ ነጻነት ላይ ተደጋጋሚ ወቀሳዎች ስለሚቀርብባቸውና ለበርክታ አመታትም በስልጣን ላይ በመቆየታቸው ምክኒያት እንደነበር ይጠቀሳል። ከዚሁ ጋር ተቃዋሚዎች ከመቸውም ጊዜ ይበልጥ በአሁኑ ወቅት ተሰባስበውና ተባብረው በሚስተር ከሚል ኪልክዳሮግሉ መሪነት  ለምርጫ የቀረቡበት ግዜ ነው ስለተባለም፤ እውነትም የፕሬዝድንት ኤሮድጋን የልስጣን ግዜ የተቃረበ መስሎ ነበር።፡

ሁለቱም ተወዳዳሪዎች  በምርጫ ዘመቻዎቻቸው ወቅት  ድጋፍ ያስገኝልናን ያሉዋቸውን ወቅታዊ አጀንዳዎችን በማንሳት ጠንክራ ቃላትን ጭምር በምጠቀም ሲያስተጋቡ ተውስተውለዋል። በቱርክ ከአራት ሚሊየን በላይ ስደተኖች ያሉ ሲሆን፤ በተለይ ሚስተር ኪሊክዳሮግሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኖችን ባአንድ አመት ወስጥ አባርራለሁ ማለታቸው ጭምር  ተሰምቶ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ቢመረጡ ኢኮኖሚውን እንደሚያሻሽሉና ከምዕራባውያን ጋር ያለውን ግንኙነትም የትሻለ እንደሚያደርጉ ደጋግመው ሲናገሩ ተስምቷል።
 
ቱርክ በአሁኑ ወቅት ካለባት  የኢኮኖሚ ችግርና  ፕሪዝዳንት ኢርዶጋንም ለበርካታ አመታት በስልጣን ከመቆየትቸው አንጻር የምርጫው ውጤት አነጋጋሪ መሆኑ ግን አይካድም። ምርጫው ነጻ የነበር መሆኑ የሚታመን ሲሆን፤ ከመራጩ ህዝብም 85 ከመቶ የሚሆነው እንደመረጠ ተጠቅሷል ። በዚህ ሁሉ መሀል ፕሬዝዳንት እርዶጋንና ፓርቲያቸው ዛሬም ያሸነፉባቸው ምክኒያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? ጋዜጠኛ ሜህሜት ሲሊክ ሁለቱን ይጠቅሳል፡ “ አንዱ ቱርክ ባለፉቱ ሁለት አስርት አመታት በኢኮኖሚ፣ በመሰረታዊ ግንባታ የተደረጉት ለውጦችና በውጭ ግንኙነትም ከተራ ተዋናይነት ወደ ተጽኖ ፈጣሪ አለም አቀፍ ሀይል መሸጋገሯ ሲሆን፤ ሁለተኛው አገሪቱ አሁን የገጠመቷን ችግሮች ልትወጣ  የምትችለው በፕሬዝዳንት ኢርዶጋን አመራር መሆኑን መራጩ ህዝብ በማመኑ እንደሆነ ይገልጻል። 
 
ቱርክ የስሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪድን ድርጅት ኔቶ ዋና አባል፤ ለአውሮጳና ለምራባውያን ባጠቃላይ ደግሞ ጠቃሚ ወዳጅ አገር እንደሆነች ቢታመንም፤ በዚያው ልክ በእነዚሁ ወዳጆቿ  በተለይ መሪው ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን አስቸጋሪ እንደሆኑ ነው የሚነገረው። አባል የሆነችበት ኔቶና አውሮጳውያኑ በዩክሬን ምክኒያት ዋና ጠላት ካደረጓት ሩሲያ ጋር ጥሩ የሚባል ግንኙነት አላት፤ በሩሲያ ላይ የተጣለውንም ማዕቀብ አትቀበልም፤ የስዊድንን የኔቶ አባልነት ጥያቄ አግዳ አቆይታዋለች። ታዲህ በዚህ ሁኒታ በሚስተር ኤርዶጋን ቀጣይ ዘመን   የቱርክና አጋሮቿ ግንኙነት እንዴት ይቀጥላል የሚለው ዋና ጥይቄ ሆኖ መቷል።። ጋዜጠኛ ጁሊያ ሃሃን እንደምትለው ምራባውያን ያላቸው ምርጫ ከፕሪዝዳንት ኢርዶጋን ጋር ተስማምቶ መስራት ብቻ ነው። “ ቱርክ ዋና የምራባውያን አጋር አገር ናት። ሆኖም ግን ከአሜሪካ፣ ከአውሮጳ ህብረትና ከኔቶ ጋር ባለፉት እመታት የነበረው ግንኙነት አስቸጋሪ ነው የነበረው። ከእንግዲህ በብራስልስ፤ ዋሽንግተን፤ ፓሪስ ያሉ ፓለቲካኞች ማድረግ ያለባቸው ሰውየው፤ ለሚቀጥሉት አምስት አመታትም በስልጣን የሚቆዩ መሆኑን ተገንዝበው ተስማምተው መስራት የሚቻልበትን ዘዴ መፈለግ ብቻ ነው፤  በማለት ቱርክ ተፈላጊና የምትተው አገር አለመሆኗንን ያገናዘበ ፖሊሲ መከተል እንደሚገባ ስገንዝበዋል። 
ገበያው ንጉሴ
 

Berlin | In Deutschland lebende Türken feiern den Wahlsieg von Recep Tayyip Erdogan
ምስል Omer Messinger/Getty Images
Türkei Wahlen Erdogan wieder gewählt
ምስል Depo Photos/IMAGO