1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተፈጥሮ አደጋ በስሎቬንያ፣ ኦስትሪያ እና ክሮኤሺያ

ሰኞ፣ ነሐሴ 1 2015

በስሎቬንያ፣ ኦስትሪያ እና ክሮኤሺያ ነፋስ በቀላቀለ በከባድ ዝናብ እና፣ ጎርፍ ብሎም የመሬት መንሸራተት ምክንያት ቢያንስ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ። በዚህ አደጋ ምክንያት የመብራት መቆራረጥ እና የጉዞ መስተጓጎልን አስከትሏል። ስሎቬኒያ ዉስጥ የደረሰዉን አደጋ ተከትሎ መንግሥት የአውሮጳ ህብረትንና «ኔቶ» ለሀገሪቱ ርዳታ እንዲያደርጉ ተማፀነ።

https://p.dw.com/p/4UsGK
Slowenien | Überschwemmungen
ምስል Fedja Grulovic/REUTERS

በስሎቬንያ፣ ኦስትሪያ እና ክሮኤሺያ ነፋስ በቀላቀለ በከባድ ዝናብ እና፣ ጎርፍ ብሎም የመሬት መንሸራተት ምክንያት ቢያንስ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ። በዚህ አደጋ ምክንያት የመብራት መቆራረጥ እና የጉዞ መስተጓጎልን አስከትሏል። 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ስሎቬኒያ ዉስጥ ባለፉት ቀናት የደረሰዉን ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተት ተከትሎ የስሎቬኒያ መንግሥት የአውሮጳ ህብረትን እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ሃገራት ድርጅት «ኔቶ» ለሀገሪቱ ርዳታ እንዲያደርጉ ተማፀነ።

STA የተባለ አንድ የስሎቬኒያ የዜና ወኪል እንደዘገበዉ ከሆነ የአውሮጳ ህብረት የሲቪል ጥበቃ ድርጅት፤ ለስሎቬንያ  30 ከባድ የመግልበጫ መሳርያዎች 30 ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎችን እና የባለሞያ ቡድን እንዲቀርብ ጠይቃለች።  ከዚህ ሌላ ስሎቬንያ ለኔቶ እና ለአዉሮጳ ህብረት እንዲቀርቡላት ከጠየቀችዉ ዝርዝር መካከል 20 ተገጣጣሚ ድልድዮች እና 200 የነፍስ አድን ወታደሮች ይገኙበታል። ባለፉት ቀናት በስሎቬኒያ በደረሰዉ ከፍተኛ ጎርፍ እና የመሪት መንሸራተት አደጋ የስሎቬንያ ሁለት ሦስተኛው ህዝብ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።  ስሎቬኒያ የደረሰባትን ይህን የተፈጥሮ አደጋ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ጎሎብ በአጠቃላይ ጉዳቱ ከ 500 ሚሊዮን ዩሮ በላይ መገመቱን ተናግረዋል።

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ