1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተሻሻለው የጸረ ሽብር አዋጅ

ዓርብ፣ የካቲት 22 2011

የተሻሻለው የጸረ ሽብር አዋጅ ለጠቅላይ አቃቤ ሕግ ሊቀርብ ነው። ሰላማዊ ሰልፍ እና የሥራ ማቆም አድማ በሽብር የማያስከስሱ ተግባራት መሆናቸውን በማሻሻያው አካትቷል።

https://p.dw.com/p/3EK1O
Anti-Terrorismus Proklamation Titelseite
ምስል DW/S. Muchie

«ካለፈው ግንቦት ወዲህ ማሻሻያው ሲሠራ ነበር»

የሕጉ አጠቃላይ ይዘት ሰፊ ችግር የነበረበትና አተገባበሩም ሃሳባቸውን በመግለጽ ላይ ያተኮሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችንና  መንግሥትን ይተቹ የነበሩ አካላትን ለማፈን ጥቅም ላይ ውሏል ያለው ግብረ ኃይሉ አዲሱ የለውጥ ኃይል ይሻሻሉ ብሎ ካስቀመጣቸው የሲቪክ ማኅበራት ማደራጃ እና የሚዲያ ሕጎች በመቀጠል እንዱ የሆነው የጸረ ሽብር ሕግ መሰረታዊ በሚባል ደረጃ ተሸሽሏል ብሏል።
ከግንቦት 2010 ወዲህ ሰፊ ጊዜ ወስዶ የተሸሻለው ይህ ሕግ የአዋጁ መንፈስም ይሁን ድንጋጌዎች፤ ከዓለም አቀፍ ሕጎች ጋር እንዲጣጣሙ፤ ሰላማዊ ሰልፍ እና የሥራ ማቆም አድማ በሽብር የማያስከስሱ ተግባራት መሆናቸውን በማሻሻያው አካትቷል።
ከዚህ በፊት አስፈጻሚው አካል እና ምክር ቤት ብቻቸውን ከተስማሙ አንድን ድርጅት አሸባሪ ብለው ይፈርጁ የነበረበትን ድንጋጌም በማሻሻያው እንዲነሳ አድርጓል። በተመሳሳይ የፍትህ አካላት ማንኛውንም በሽብር የጠረጠሩትን ግለሰብ ስልክ መጥለፍ እና ልዩ ክትትል ማድረግ የሚፈቅደውን አንቀጽ በማንሳት አስገዳጅ ከሆነም በፍርድ ቤት ትእዛዝ ብቻ እንዲከናወን የሚል የማሻሻያ ሃሳብ አስፍሯል።
ረቂቅ የማሻሻያ አዋጁ በቀጣይ ከፍትህ እና ጸጥታ አስከባሪ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወደ ሚኒስትሮች ምክርቤት ከዚያም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡።

ሕጉ የሚጸድቅ ከሆነም እንደቀደመው ጊዜ አተገባበሩ እና አፈጻጸሙ ባልተገባ አኳኋን እንዳይሆን የአስፈጻሚ አካላትና ተቋማት አቅም እንዲጠናከር፤ ሲቪክ ማህበረሰቡም ሕጉን በንቃት እዲከታተለው ተጠይቋል።

ሰለሞን ሙጬ
ነጃት ኢብራሒም
ማንተጋፍቶት ስiሺ