1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብርን የምንዛሪ ተመን በኮሮና ዘመን ማዳከም ያዋጣል?

ረቡዕ፣ ግንቦት 5 2012

የዓለም የገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ብር ከዶላር አኳያ ያለውን የምንዛሪ ተመን እንድታዳክም እየጎተጎቱ ነው። የምጣኔ-ሐብት ባለሙያዎች ግን እንዲህ አይነት እርምጃ የከፋ የዋጋ ግሽበት ሊያስከትል እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ። ለመሆኑ የኢትዮጵያም ሆነ የዓለም ገበያ በኮሮና ወረርሽኝ በተቃወሰበት በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት እርምጃ ያዋጣል?

https://p.dw.com/p/3cAwL
Geldscheine
ምስል DW/E. Bekele Tekle

የብርን የምንዛሪ ተመን በኮሮና ዘመን ማዳከም ያዋጣል?

የዓለም የገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎች ኢትዮጵያ የብርን የምንዛሪ ተመን እንድታዳክም ግፊት እያደረጉ መሆኑን ራሱ የዓለም የገንዘብ ድርጅት በዚህ ወር መጀመሪያ ባወጣው ዘገባ ጠቁሟል። ድርጅቱ ብር በተለይ ከዶላር አኳያ ያለውን የምንዛሪ ተመን ማዳከም በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ የሚፈጠርን ችግር ለመቋቋም ያስችላል ብሏል። 

በዚያው በዓለም የገንዘብ ድርጅት ሰነድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት በመደበኛ እና ኢ-መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ግብይት መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ እና በሒደት በገበያ አቅርቦት እና ፍላጎት ወደሚመራ የግብይት ሥርዓት ለመቀየር ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል። ነገር ግን ባለሥልጣናቱ እርምጃውን ሲወስዱ ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ መናገራቸው ተገልጿል። 

የዓለም የገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የብር የምንዛሪ ተመን ቀስ በቀስ በማዳከም በባንኮች በሚከወነው እና በጎንዮሽ ግብይት መካከል የነበረውን ልዩነት ማጥበብ ችለዋል ብሏል። በሁለቱ ግብይቶች መካከል በኅዳር ወር 35 በመቶ የነበረው ልዩነት በሚያዝያ አጋማሽ ወደ 27.5 በመቶ ዝቅ እንዳለ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ሰነድ ጠቁሟል። የዓለም የገንዘብ ድርጅት እንዳለው በዚህ የኢትዮጵያም ሆነ የዓለም ገበያ በተቃወሰበት ወቅት የብር የምንዛሪ ተመንን ማዳከም ያዋጣል?

የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያ እና የምጣኔ-ሐብት ተንታኙ አቶ አብዱልመናን መሐመድ በጉዳዩ ላይ ለዶይቼ ቬለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ


እሸቴ በቀለ 
አዜብ ታደሰ