1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡድን ሰባት ሀገራት በአፍሪካ መዋዕለ-ንዋይ እና መሠረተ-ልማት ለማስፋፋት ቃል ገቡ

Eshete Bekeleሰኞ፣ ሰኔ 10 2016

በኢንዱስትሪ የበለጸጉት የቡድን ሰባት ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ በሰባት ሀገራት ተግባራዊ የሚደረግ “ኢነርጂ ለአፍሪካ ዕድገት” የተሰኘ መርሐ-ግብር እንደሚጀምሩ ገልጸዋል። “በጠንካራ የአፍሪካ ሀገራት ባለቤትነት” ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ዕቅድ “ዘላቂ፣ የማይበገር እና አካታች ዕድገት እና የኤኮኖሚ ልማት” ለመፍጠር ውጥን አለው። ባለፈው ሣምንት የተካሔደው የቡድን ሰባት ስብሰባ ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ የሚደረግ ስደት ላይ ጭምር መክሯል

https://p.dw.com/p/4h9qD
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

DW-Interview mit Frank-Walter Steinmeier
ምስል DW/R. Oberhammerምስል DW/R. Oberhammer

ማሕደረ ዜና

ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ