1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀይ ባህር አፋር ድርጅት መግለጫ

ሰኞ፣ ነሐሴ 20 2005

የድርጅቱ አመራር አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ የኤርትራ መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት በሚወስዳቸው እርምጃዎች የቀይ ባህር አፋሮችን እንደሚገድል እንደሚያስርና ከቀያቸው እንዲሰደዱ እንደሚያደርግ ተናግረዋል ።

https://p.dw.com/p/19WOo
ምስል picture-alliance/dpa

የኤርትራ መንግሥት ባለፈው ሐምሌ አጋማሽ ላይ ወደ የመን በመጓዝ ላይ የነበረች አንዲት አነስተኛ መርከብ በሚሳይል መጥቶ በውስጧ የነበሩትን 28 የቀይ ባህር አፋር ወጣቶችን ገድሏል ሲል የቀይ ባህር አፋር ተራድኦ ድርጅት አስታወቀ ። የድርጅቱ አመራር አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ የኤርትራ መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት በሚወስዳቸው እርምጃዎች የቀይ ባህር አፋሮችን እንደሚገድል እንደሚያስርና ከቀያቸው እንዲሰደዱ እንደሚያደርግ ተናግረዋል ። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኘው የአዲስ አባባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል ።
የቀይ ባህር አፋር ተራድኦ ድርጅት ስላወጣው መግለጫ የኤርትራን መልስ ለማግኘት ለኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ ደውለን ወደ ኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መርተውን ነበር ። ሆኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣናትን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ