1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሽግግር ፍትሕ በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ የካቲት 29 2015

በሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ የሲቪክ ድርጅቶች እና የዴሞክራሲ የሚባሉ ሌሎች ተቋማት ዛሬ ተወያይተዋል።በዚሁ ወቅት ያገኘናቸው ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ የተባለ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞገስ በቀለ ውጥኑን በበጎ የሚታይ ብለውታል።

https://p.dw.com/p/4OPNR
Äthiopien Addis Ababa | Nationales Konsultationsprogramm
ምስል Solomon Muche/DW

የሽግግር ፍትሕ ጥፋተኞች ተጠያቂ እንዳይሆኑ ያደርግ ይሆን?

"የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አማራጭ"  የተባለዉ መርሕ ግቡን እንዲመታ  ሐገሪቱ "በሴራ ከተተበተበ የፖለቲካ ዐውድ" መላቀቅ እንደሚገባት በጉዳዩ ላይ የሚወያዩ ጠየቁ።የኢትዮጵያ መንግስት ያዘጋጀዉ "የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አማራጭ» በግጭትና ጦርነት የተፈፀሙ በደሎችን ለማከም የሚረዱ መፍትሔዎችን የሚሰጥነዉ ይባላል።ባለፈዉ ሰኞ በተጀመረዉ ዉይይት ላይ የሚካፈሉ የተወሰኑ የሲቪክ ማሕበራት ተወካዮች የሕግ የበላይነት እንዲከበር እና ውጥኑ በገለልተኛ አካል እንዲፈፀም ጠይቀዋል።

በሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ የሲቪክ ድርጅቶች እና የዴሞክራሲ የሚባሉ ሌሎች ተቋማት ዛሬ ተወያይተዋል።በዚሁ ወቅት ያገኘናቸው ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ የተባለ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞገስ በቀለ ውጥኑን በበጎ የሚታይ ብለውታል።
ቪዥን ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ የተባለ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ታደለ ደርሰህ ደግሞ ይህ ውጥን እውን እንዲሆን ከሆን የፖለቲካ ሥርዓት ዐውድ ለውጥ ያስፈልጋል።የሽግግር ፍትሕ አጥፊ ናቸው ተብለው በሚለዩ ወገኖች ሁሉ ላይ ዓለም አቀፍ ተጠያቂነት እንዳይኖር ያደርግ ይሆን ለሚለው ጥያቄ የሰነዱ አዘጋጆች ይህ እንደማይሆን ምላሽ ሰጥተዋል።  አቶ ሞገስ በቀለም ይህንኑ ያጠናክራሉ።
የኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሄኖክ መለሰ በሥራቸው የሚገኙ ከ 4 ሺህ በላይ የሲቪክ ድርጅቶች የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ እንዲሳካ ግፊት እንዲያደርጉ፣ መንግስትም የሚደረገውን ግፊት በበጎ እንዲመለከት ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተንሰራፍታል።
አለመረጋጋት ፣ ግጭትና የእርስ በርስ ጦርነት ሞትና መፈናቀል እንዲጨምር አድርጓል።የጥፋቶች ማህበረሰባዊ ቅርጽ መያዝም በመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት እና አካሄድ ፍትሕ መስጠትንም ሆነ ይቅርታ እና እርቅን ማከናወንን አላስችል በማለቱ የሽግግር ፍትሕን መተግበር የግድ ማስፈለጉ ታምኖበታል።
ይህ ውጥን ምን ያህል ይሳካል የሚለው ግን ወደፊት የሚታይ ነው።

Äthiopien Addis Ababa | Nationales Konsultationsprogramm
ምስል Solomon Muche/DW

ሰሎሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ