1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያዉ ፕሬዝደንት የኤርትራ ጉብኝት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 6 2014

ምንም እንኳ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት ባይቀበሉትም፤ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ግን፤ ከአኢትዮጵ መንግስት ጋር በተካሄደው ጦርነት የሶማሊያ ምልምል ወታደሮች ከኤርትራ መንግስት ወታደሮች ጎን ተሰልፈውና ለኢትዮጵያ መንግስት አብረው ተዋግተዋል በማለት ክስ ሲያቀርብ ነው የቆየው

https://p.dw.com/p/4E58V
Somalia Hassan Sheikh Mohamud
ምስል Feisal Omar/REUTERS

አዲሱ የሱማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሳን ሼክ ማህሙድ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ኤርትራን ለአራት ቀን ጎብኝተዋል።ፕሬዝደንት ሐሰን ከአስተናጋጃቸዉ ከኤርትራዉ ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ሆነዉ ኤርትራ ባሰለጠነቻቸዉ  የሶማሊያ ወታደሮች የምረቃ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።የሶማሊያ ወታደሮች ለስልጣና ወደ ኤርትራ መላካቸዉ ሶማሊያ ዉስጥ የተለያዩ ጥያቄዎችን አስነስቷል።ለስልጠና ወደ ኤርትራ የተላኩት ወታደሮች ሁኒታ  በሀገር ውስጥ በርክታ ጥያቄዎችን ሲያስነሳ የቆየ አጀንዳ ነው። ምንም እንኳ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት ባይቀበሉትም፤ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ግን፤ ከአኢትዮጵ መንግስት ጋር በተካሄደው ጦርነት የሶማሊያ ምልምል ወታደሮች ከኤርትራ መንግስት ወታደሮች ጎን ተሰልፈውና ለኢትዮጵያ መንግስት አብረው ተዋግተዋል በማለት ክስ ሲያቀርብ ነው የቆየው። የቂድሞው የሶማሊያ ፕሬዝድንት ሚስተር ሞሀመድ አብዱላሂ በቅጽል ስማቸው ፎርማጆ ባለፈው ሰኔ ወር ስልጣናቸውን ለተመራጩ ፕረዝዳንት ሃሳን ሼክ ማህሙድ  ሲያስክረክቡ ግን፤ በኤርትራ አምስት ሺ የሶማሊያ ወታደሮች በስልጠና ላይ መሆናቸውን ገልጸው ነበር፡፤ የአሁኑ የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት ዋና ትኩረተትም ይኸው በኤርትራ የስለጠኑት ወታደሮች ጉዳይ እንደሆነ ነው የፖለቲካ ተንታኖች የሚናገሩት። 
በዓለማቀፉ የግጭቶች ተንታኝ ድርጅት (ክራይሲስ ግሩፕ) የምስራቅ አፍርካ ተመራማሪ የሆኑትን ሚስተር ኦመር ማህሙድን ዶቼ ቬለ ዲደብሌው ራዲዮ ስለ ፕሬዝዳንት ህሳን የኤርትራ ጉብኝትና የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ማብራሪያ ጠይቆ ነበር ። ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ በፕሬዝዳንት ሀሣን የሹመት በዓል ካልተገኙት የአክባቢው አገሮች መሪዎች አንዱ እንደነበሩና ፤ ከአዲሱ የሱማሊያ ፕሬዝዳንት ጋር ያላቸው ግንኑነት ጥሩ የሚባል እንዳልሆነ ሲገለጽ የቆየ ሆኖ ሳለ፤ ሚስተር ሀሰን ግን በመጀመሪያ ከጎበኙዋቸው አገሮች ኤርትራን አንንዷ ማድረጋቸው  ምን ትርጉም ይኖረዋል?  የሚል ነበር የመጅመሪያው ጥያቄ፤  
 “የጉብጅቱ የመጀመሪያውና ትልቁ ነገር የሚመስለኝ በፕሬዝዳንት ፎርማጆ ዘመን በኤርትራ ሲሰለለጥኑ የቆዩት የሶማሊያ ወታደሮች ጉዳይ ነው። በኤርትራ የሶማሊያ ሰልጣኝ ወታደሮች ጉዳይ ሚስጥራዊና ብዙም የማይታወቅ ሆኖ ቆቷል። ፕሬዝዳንት ሼክ ማህሙድ ወደ ኤርትራ በመሄድ የወታደሮቹን ስልጠና ማየትና ወደ አገራቸው ተመልሰው ያገሪቱ ሰራዊት አካል የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት የመጀመሪያው ስራቸው ማድረጋቸውን የሚያሳይ ነው ጉብኝቱ ብለዋል። 
በመቀጠል በኤርትራ የሱማሊያ ሰልጣኝ ወታደሮች ከኤርትራ ሰራዊት ጋር ሆነው ህወሀትን  የመዋጋታቸውን ክስ ያጠራ ይሆን ወይ? ተብለውም ነበር ሚስተር ኦማር፤ “ ልክ ነው ብዙ ግልጽ ያልሆኑ ነገሮች አሉ። ግን ይህ ጉብኝት ሁኒታውን ለማጥራት የመጅመሪይው እርምጃ ሊሆን ይችላል። አሁን ቢያንስ ወታደሮች በስልጠና ላይ መሆናቸው ታይቷል። ቢሆንም ብዙ የሚነሱ ጥያቄዎች፤ ለምሳሌ ለምን ስልጠናው ይህን ያህል ግዜ ወሰደ? የሚለውና ሌሎችም የሚነሱ ጥያቄዎች አሉ፤ በማለት ሆኖም ጉብኝቱ ለጥያቄዎቹ መልስ የመጀመሪያው እርምጃ ሊሆን እንደሚችል አብራርተዋል  
ጉብኝቱ በጠቃላይና ሁለቱ መሪዎች የደረሱበት  ስምምነትና የፈረሙት የመግባቢያ ስነድ ለዓፍሪካ ቀንድ ሰላም ያለውን ፋይዳና በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሂዱ ባሉት ግጭቶች ላይ ስለሚኖረው አንደምታም የተጠየቁት  ሚስተር ኦማር፤ ጉብኝቱም ሆነ የተደረሱት ስምምነቶች በዋናነትት የሁለቱን አገሮች ግንኑነት የሚመለክት መሆኑን አውስተው፤ ኤርትራ በወታደርዊውና ደህንነቱ ዘርፍ የምትሰጠውን እርዳታና እገዛ ስለምትቀጥልበት ሁኒታ ትኩረት የሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል 
በሶማሊያ ጠንካራ መንግስት እንዲመስረትና ሰላም እንዲፈጠር በሚል እጁን ያላስገባ የውጭ ሀይል እንደሌለ የሚታወቅ ሲሆን፤ የአውርፓ ህብረት፣ አሜሪካ፣ የገልፍ ባህረ ሰላጤ አገሮች፤ ቱርክ፤ ግብጽና ጎረቤቶቿም በሱማሊያ ጉዳይ ያገባናል ባዮች ናቸው፡፤ ግን እስካሁን ሱማሊያ ከችግር አልተላቀቀችም፤ አሁንም ጠንክራ መንግስት የላትም፤ በአሸባሪዎች በየዕለቱ እየተናወጠች ነው። ይልቁንም የነዚህ አገሮች ጣልቃ ገብነትና ፉክክር የችግሩ አካል ሆኖ ይሆን? የመጨረሻው ለሚስተር ኦማር የቀረበ ጥያቄ ነበር፤ “  ይህን ችግር አዲሱ ፕሬዝዳንት በደንብ የተረዱት የመስለኛል። የምርጫ ዘመቻው ዋና መፈክር    “ሰላም ከውስጥም ከውጭም” የሚል ነበር በማለት፤ እንደሚመስለኝ ሼኩ የሱማሌን ጥቅም በሚመለክት ከሁሉም ጋር ወዳጅ በመሆን በጥንቃቄ አብሮ ለመስራት ያሰቡ ይመስለኛል ብለዋል  
ገበያው ንጉሴ 

Somalia Präsident Hassan Sheikh Mohamud
ምስል Farah Abdi Warsameh/AP/picture alliance
Äthiopiens Premierminister Abiy Ahmed, Eritreas Präsident Isaias Afwerki und Somalias Präsident Mohamed Abdullahi Mohamed
ምስል Eduardo Soteras/AFP/Getty Images

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ