1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመስከረም 6 ቀን 2017 የስፖርት ዝግጅት

ሰኞ፣ መስከረም 6 2017

ቡድኑ ካስመዘገበው እና ካያሳየውን ውጤት ይልቅ የተፈጠረው ውዝግብ ከፍተኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆንዋል ።

https://p.dw.com/p/4kgle
Paris 2024 Marathon Tamirat Tola Äthiopien
ምስል JOEL CARRETT/AAP/IMAGO

የመስከረም 6 ቀን 2017 ስፖርት

ባለፉት ተከታታይ የኦሎምፒክ ውድድሮች ኢትዮጵያን ወክሎ የሚጓዘው ቡድን  ያሳየው ውጤት  ከተጠበቀው በታች ዝቅተኛ  ነው።  ለዚህ የውጤት ማነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተጠያቂ መሆን አለባቸው ። ኢትዮጵያ በተከታታይ በደረገቻቸው ኦሎሚክ ውድድርዎች ለመጣው  ዝቅተኛ ውጤት ተጠያቂ ይሆናሉ የተባሉ ሁለት አካላት ላይ ክስ ቀርቦ እንደነበር ይታወሳል። በኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ  ላይ።ሌላ በኩሉ የስፖርት ነክ ጉዳዮች በመደበኛ ፍርድ ቤት  ሊታይ አይችሉም ይህ  ሄዶ ሄዶ በእግርኳሱ እንደተቀጣነው ሁሉ አሁንም በኦሎምፒክ  እስከመታገድ ያደርሰናል የሚሉም አልጠፉም።

 በየአራት አመቱ የሚደረጋውን የኦሎፒክ ውድድር የሚሳተፈው የ ኢትዮያ ቡድን ድል ከራቀው ሰንብቷል  በተለይ በለንደን በቶኪዮ በቅርቡ ደግሞ በፓሪስ በተካሄደው የአለም ኦሎምፒክ ውድድር ላይ ተካፋይ የሆነው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ውጤት አብዛኛውን ህዝብ ያስደነገጠ ነበር። ቡድኑ ካስመዘገበው እና  ካያሳየውን ውጤት ይልቅ የተፈጠረው ውዝግብ ከፍተኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆንዋል ። ኢትዮጵያ በሚቀጥለው የሎስአንጀለሱ ኦሎምፒክ ከመሳተፏ በፊት የውስጥ ችግሮቹ መፈታት አለባቸው የሚሉ ወገኖች ይመለከታቸዋል ያሉዋቸውን  ሁለት  አካላት ላይ ክስ መስርተዋል።

ክስ የመሰረቱት የ ኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሪሽን የቴንስ ፊዴሪሽን  አትሌት ሀይሌ ገስላሴ እና አትሌት ገዛሀኝ አበራ ናቸው። ሀገርን በሚወክሉ የስፖርት ውድድሮች የሚያመጣው አሉታዊም ሆነ  አወንታዊ ጫና በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይመለከታል።  በሌላ በኩሉ የስፖርት ነክ ጉዳዮች በመደበኛ ፍርድ ቤት አይታዩም ይባላል DW ያነጋገራቸው  የህግ ባለሙያ ተከታዮን ብለዋል።  

"እኛ እንኩዋን በህይወት እያለን ባንኖርም ከአትሌቲክሱ ጋር አብረን አለን ። የአበበን ድል አሁን እንደምንዘክር ሁል ስለዚህ የተሻለ ወጤት ለማምጣት የምንችለውን ሁሉ ከማድረግ ወደሁዋላ አንልም" ሲል ለ DW የተናገርው  ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ነው። 

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር መሰረት ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ ይገኛል። ሀገር የሚያኮራ ውጤት እንዲመጣ ተቆጥሮ እና ተለክቶ  የተሰጠውን ስራ  እና ሀላፊነት ሰርትዋል ። አሁንም ከመስራት ወደኃላ አይልም። ለውጤት መታጣቱ  ተጠያቂ ልንሆን አይገባም ሲሉ  ለ DW  የተናገሩት የኢትዮጵያ ኦሎፒክ ኮሚቴ  ዋና ፅሀፊ  አቶ ዳዊት አስፋው ናቸው ።

የስፖርት ጋዜጠኛው ፍቅር ይልቃል  እኔ እንደባለሙያ የምጠብቀው ይሄ ሁሉ ውዝግብ ሀገርን ዋጋ ከማስከፈሉ በፊት የሚመለከታቸው አካላት የተሻለ መስራት ለሚችሉ ሰዎች ቦታወን ይላቃሉ ብዬ ነው ይላል። ከ ኦሎፒክ ስፖርቶች ጋር በተያያዘ በሀላፊነት በተቀመጡበት ሁሉ ጨምሮ ሁሉም የ ኦሎፒክ ስፖርቶች በግልፅነት እና በታማኝነት  መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ካልሰራይ በስተቀር  በየግዜው ውጤት ማጣትን ተከትሎ የሚመጣ ውዝግብ መፍትሄ አይኖረውም ሲል ጋዜጠኛ ግርማቸው እንየው ለDW ተናግርዋል 

Paris 2024 | Sifan Hassan gewinnt den Frauen Marathon
ምስል Christian Petersen/Getty Images

በሌላ የአትሌቲክስ ዜና

በ5 ሺህ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በመግባት አሸነፉ። በብራሰልስ በተካሄደው የ2024 ዳያመንድ ሊግ 5 ሺህ የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ አሸንፈዋል ።አትሌት በሪሁ አረጋዊ 12:43.66 በሆነ ሰዓት በመግባት በውድድሩ ቀዳሚ ሆኖ ጨርሷል ። ሀጎስ ገብረህይወት 12:44.25 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ እንዲሁም ጥላሁን በቀለ 12:45.63 በሆነ ሰዓት በመግባት ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሌግ

እሑድ በተካሄደው የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ጨዋታ የሰሜን ለንደን ተቀናቃኞቹ ቶተንሃም እና አርሰናል ተገናኝነተው መድፈኞቹ ድል ቀንቷቸዋል።

በ64ኛው ደቂቃ የመሃል ተለከላካዩ ጋብርኤል  በግንባሩከመረብ ባገናኛት ኳስ የሚኬል አርቴታ ቡደን መሪ እንዲሆን አሰችሏል። ጨዋታው በዚህ ብቸኛ ጎል የተጠናቀቀ ሲሆን አርሰናል ወሳኝ ሶስት ነጥቦችን ይዞ ተመልሷል።

በሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች አርሰናል ቶትንሀምን  አሸንፎ በደርቢው ያለውን የበላይንት አሳይቷል።

በተመሳሳይ ጨዋታ  በርንማውዝ በ ኒውካስል 2ለ1 ተረትዋል
ሃና ደምሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ፀሐይ ጫኔ