1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

DW Amharic የሰኔ 16 ቀን 2016 የዓለም ዜና

Eshete Bekeleእሑድ፣ ሰኔ 16 2016

በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ ሶማሌ፣ አፋር እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ለ6ኛው ሀገር አቀፍ የቀሪ እና የድጋሚ ምርጫ ነዋሪዎች ድምጽ ሲሰጡ ዋሉ። ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ መንግሥታቸው ተግባራዊ በሚያደርገው የግብር ጭማሪ ላይ በኬንያ ሀገር አቀፍ ተቃውሞ ካካሔዱ ወጣቶች ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን አስታወቁ። የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮቭ ጋላንት ከመስከረም 26 ቀን 2016 ጀምሮ በጋዛ ሲካሔድ በቆየው ውጊያ ላይ “ወሳኝ” ለተባለ ንግግር ወደ አሜሪካ አቀኑ። የኬንያ ኃይሎች ማክሰኞ በወሮበሎች ወደምትታመሰው ሔቲ እንደሚዘምቱ የሀገሪቱ መንግሥት እና የፖሊስ የመረጃ ምንጮች ተናገሩ። በሩሲያ እና ዩክሬን ጥቃቶች ሰዎች ተገደሉ

https://p.dw.com/p/4hPNB
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

PODC-DW-Amharisch-News-DWcom

የዓለም ዜና

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና የዜና ትንታኔዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ።