1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 9 2014

ሰሞኑን በደቡብ ወሎ ዞን አንዳንድ አካባቢዎች በአዲስ በተቀሰቀሰው ጦርነት ብቻ ከ250 ሺህ በላይ ወገኖች መፈናቀላቸውን በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን አስታወቀ። በአማራ ክልል በጦርነት ቀጠና 4 ሚሊዮን ህዝብ የሚገኝ ሲሆን የተፈናቃዮች ቁጥር ደግሞ አጠቃላይ ወደ 1 ሚሊዮን 700ሺህ ማደጉን ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/41rzV
Bahir Dar | Binnenflüchtlinge aus Waghemra
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

«በዋግህምራ ደግሞ ኅብረተሰቡ ለረሃብ ተጋልጧል»

ሰሞኑን በደቡብ ወሎ ዞን አንዳንድ አካባቢዎች በአዲስ በተቀሰቀሰው ጦርነት ብቻ ከ250 ሺህ በላይ ወገኖች መፈናቀላቸውን በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን አስታወቀ። አጠቃላይ በጦርነቱ የተፈናቀሉት ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን መብለጡን ክልሉ አመልክቷል።  በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ደግሞ የመሰረታዊ ሸቀጦች እጥረት ነዋሪዎችን ለርሀብ ዳርጓል ተብሏል። በጦርነት ቀጣና ያሉ ከ4 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ዓለም አቀፉ ረጂ ድርጅት አስካሁን መድረስ እንዳልቻለም ባለስልጣናቱ አመልክተዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን 

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ