1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰላም ቀን በጁባ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 22 2011

በርስበርስ ጦርነት የደቀቀችው ደቡብ ሱዳን ትናንት የሰላም ክብረ በዓል በደማቅ ሥነ ሥርዓት በመዲናዋ ጁባ አክብራለች፡፡ የቀድሞው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የአማጺያኑ መሪ ሬክ ማቻርም ከሀገራቸው ከወጡ ከሁለት ዐመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጁባ ተመልሰው በበዓሉ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

https://p.dw.com/p/37WyM
Südsudan Rückkehr von Riek Machar
ምስል Reuters/S. Bol

መሪዎቹ ለሰላም መዘጋቸታቸውን ገልጸዋል

 በጁባው ነጻነት አደባባይ በባህላዊ ዳንስ ታጅቦ በተከበረው ሥነ ሥርዓቱ ላይ አዲሲቷ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ እንዲሁም የኡጋንዳ፣ ግብጽ፣ ሱዳን እና ሱማሊያ መሪዎችን ጨምሮ የ13 ሀገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የዐለም ዐቀፍ ድርጅቶች ልዑካን ታድመዋል፡፡ በክብረ በዓሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናዊያንም ተገኝተው ደስታቸውን ሲገልጹ ውለዋል፡፡ ቻላቸው ታደሠ  ኬንያ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ቻላቸው ታደሠ  

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ