1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርት ዋጋ መጨመር በአሶሳ

ዓርብ፣ ነሐሴ 3 2016

በአካባቢው በሚመረቱና የውጪ ምንዛሪ በማይጠቁ ምርቶች ጭምር ላይ እንደ ጤፍ፣ሽንኩርት እና ለሎች ምርቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ኣሳሳቢ መሆኑን ነዋሪዎች አስረድተዋል። ፡ በአዲስ አበባ ከተማ በ25 ብር የሚሸጠው አንድ የታሸገ 2 ሊትር ውሀ በአሶሳ ከተማ በ50 ብር አንድ አንድ ቦታዎች ላይ ደግሞ በ60 ብር እንደሚሸጥ ነዋሪዎች አስታውቋል፡፡

https://p.dw.com/p/4jIuT
Äthiopien Assosa City | Benishangul Gumuz Region
ምስል Negassa Dessalegn/DW

የምርት ዋጋ መጨመር በአሶሳ


በአሶሳ ከተማ እና አካባቢው ከሰሞኑ መሰረታዊ የፍጆታ ምርቶችና የህንጻ መሳሪያዎች ዋጋ መጨመሩን ያጋርናቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ እንደዚሁም ምርቶችን ዋጋ ለመጨመር ሲባል በግለሰቦች  ምርት እንደሚደበቅም አመልክተዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ ረቡዕ አንስቶ በመሰረታዊ የፍጆታ ምርቶች ላይ ከ 200 እስከ 500 ብር ጭማሪዎች መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ 1100 ብር የነበረ የዘይት ዋጋ እስከ 1400፣ ዱቄት ዋጋ ከ90 ብር በኪሎ 150 ብር መድረሱን ተገልጸዋል፡፡ በምርቶች ላይ የሚደረጉ ድንገተኛ የዋጋ ጭማሪዎች በነዋሪ ላይ ጫና እያሳደረ የሚገኝ መሆኑን ጠቁመው እንደዚህ ዓይነት የዋጋ ጭማሪዎችን መንግስት ተከታትሎ የማስተካያ እርምጃ መውሰድ አለበት ብሏል፡፡የፍጆታ ምርቶች ዋጋ መጨመር በአሶሳ


አሶሳ ከተማን ከኦሮሚያ እና አማራ ክልል ጋር የሚገናኙ መንገዶች አልፎ አልፎ መዘጋት በአካባው በገበያ ሁኔታ ላይ ተጽህኖ ማሳደሩን  ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አዚሁ አካባቢው የሚመረቱ እና የውጪ ሚንዛሪ በማይጠቁ ምርቶች ጭምር ላይ እንደ ጤፍ፣ሽንኩርት እና ለሎች ምርቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ኣሳሳቢ መሆኑን ያጋገርናቸው ነዋሪዎች አብራርተዋል፡፡የምርቶች ዋጋ ጭማሪ በአዲስ አበባ

በአዲስ አበባ ከተማ በ25 ብር የሚሸጠው አንድ የታሸገ 2 ሊትር ውሀ በአሶሳ ከተማ በ50 ብር አንድ አንድ ቦታዎች ላይ ደግሞ በ60 ብር እንደሚሸጥ በመግለጽ በሁሉም ዓይነት ምርቶች ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ጭማሪ በየጊዜው መቀነስ አለማሳየቱን ነዋሪዎች አስታውቋል፡፡

የአሶሳ ከተማ
የአሶሳ ከተማምስል Negassa Dessalegn/DW


በከተማው ያለ አግባብ ዋጋ ጭማሪ ተደርገዋል የተባለውን የነዋሪዎች ቅሬታ አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከክልሉ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በስልክም ተቋማቸው ድረስ በመሄድም ያደረግነው ጥረት ስብሰባ ላይ ነን በማለታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡ በቅርቡ ቢሮው በማህበራዊ መገናኛ ዜዴ ት ባስተላለፈው መረጃም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራን ምክንያት በማድረግ በግብይት ላይ ህገ ወጥ ተግባር ፈጽመዋል ያላቸውን ከ3 መቶ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ በክልል ደረጃ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡ የአሶሳ የኑሮ ዉድነት

 የክልሉ መንግስት የኢኮኖሚ ሪፎርም ተከትሎ በምርቶች ላይ ያለአግባብ ዋጋ የሚጨምሩና ምርት የሚሰውሩ  አካላትን ቁጥጥር የሚያደርግ ግብረ ሐይል ማቋቋሙን የገለጸ ሲሆን ለግንባታ ስራዎች ግብአት የሚውሉ ምርቶች ዋጋም ተመን ወጥቶላቸዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ