የሜቴክ ሕገ-ወጥ የባሕር ላይ ንግድ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 4 2011ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ለ DW እንደገለጹት የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ድርጅት በእርጅና ምክንያት እንዲወገዱ እና ሜቴክ ቆራርጦ አልያም አቅልጦ ለሌላ የኢንዱስትሪ ግብአት እንዲጠቀምባቸው ግልጽ ባልሆነ የሽያጭ ውል ያስረከበውን ሁለት ግዙፍ መርከቦች ከስምምነቱ ውጭ ለሕገወጥ ንግድ በመጠቀም አገሪቱን ከ 500 ቢልዮን ብር በላይ ለተጨማሪ ኪሳራ ዳርገዋል ብለዋል:: አቶ ሱሌይማን እ.ኤ.አ እስከ 2015 ዓ.ም በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር በነበሩበት ወቅት ከ 6ወራት በላይ ያለአገልግሎት ከፍተኛ የወደብ ኪራይ እየተከፈለባቸው ከቆዩ በኋላ በሕገወጥ ንግድ የተሰማሩትን ሜቴክ የተረከባቸውን መርከቦች በተመለከተ በወቅቱ ለመንግሥት ተቃውሞዋቸውን በመግለጽ ደብዳቤ ቢጽፉም ሰሚ አካል እንዳላገኙ አመልክተዋል። ሜቴክ ከባሕረ ሰላጤው ሃገራት እስከ ሶማሊያ በርበራ ወደብ በመርከቦቹ ወታደራዊ ትጥቆችን እና የጦር መሣሪያዎችን በሕገወጥ መንገድ ይነግድ እንደነበር የሚገልጹ መረጃዎች ሲወሩ መስማታቸውንም ነው ዲፕሎማቱ ያስረዱት። ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል።
እንዳልካቸው ፈቃደ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ