1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ የካቲት 28 2016

በኢትዮጵያ የማህፀን በር መከላከያ ክትባት ለታዳጊ ሲቶች መስጠት ከተጀመረ 5ኛ ዓመቱን ይዟል። ባለሞያዎች ክትባቱ ከ90 ክመቶ በላይ በሽታውን ለመከላክል ያስችላል ይላሉ። ክትባቱ በዚህ ሳምንት በተከታታይ ለ5 ቅናት ለ14 አመት ታዳጊ ሲቶቸ በመሰጠት ላይ ነው።ሁለት ጊዜ ይሰጥ የነበረው ክትባቱ ተሻሽሎ አሁን አንድ ግዜ ብቻ ነው የሚሰጠው።

https://p.dw.com/p/4dGJX
Bangladesch HPV Impfung
ምስል Mortuza Rashed/DW

የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በዚህ ሳምንት በኢትዮጵያለ14 አመት ታዳጊ ሲቶቸ ለ5 ቅናት በመሰጠት ላይ ነው

በማህፀን በር ካንሰር የበርካታ እናቶች ህይወት ያልፋል።እሰካሁን ብዙም ባልተነገረለት የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በየአመቱ ቁጥራቸው 7400 የሚጠጋ እናቶቸ ይያዛሉ። በበሽታው ክተያዙት ሲቶቸ መካክል ክ5000 ሺህ በላይ የሚሆኑት ህይወታቸውን ያጣሉ።የማህፀን በር ጫፍ ካነሰር በአለም አቀፍ ደረጃ በበሽታው ሲታይ ደግሞ በቡeታው በየ120 ስከንድ ልዩነት  የአንዲት ሴት ሕይወት ያልፋል።የጡት እና የማሕጸን ካንሰር

የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በሀገራቸን ከጡት ካንሰር ቀጠሎ ሁለተኛው የእናቶች ገዳይ በሽታ ነው። በተለይም  እንደ ኢትዮጵያ ባሉ እጅግ  ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ከሰሃራ በታች በሚገኙ ሃገራት፤ ውስጥ  የሚኖሩ ሴቶች፤ የበለጠ ለማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭ ናችው ሲሉ አቶ መንግሥቱ ቦጋለ በጤና ሚኒስቴር የክትባት ጉዳዮች የቴክኒክ አማካሪ ለDW ተናግረዋል። 

 

በኢትዮጵያ  የማህፀን በር ጫፍ መከላከያ ክትባት  ለታዳጊ ሲቶች መስጠት ከተጀመረ 5ኛ ዓመቱን የያዘ ሲሆን  ክትባቱ 90 ክመቶ በላይ በሽታወን ለመከላክል ያስችላል ሲሉ ባለሙያው ይናገራሉ .የማህፀን ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት በአማራ ክልል

በያዝነው  ሳምንት በተከታታይ ለ5 ቅናት እድሚያች14  አመት  ለሚሆኑ ታዳጊ ሲቶቸ በመሰጠት ላይ ያለው የማህፀን በር ካነሰር መከላከያ ክትባት ከዚህ ቀደም  ሁለት ጊዜ ይስጥ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ከትባቱ ተሻሽሎ በመምጣቱ ምክንያት አንድ ግዜ ብቻ የሚስጥ ሆነዋል.ብለዋል ። ክትባቱን አስቀድሞ መውስድ በሀገራቸን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ሴቶቸ የሚያጠቃውን የማህፀን በር ጫፍ ካንሰርን ለመከላከል ሁነኛ መፍትሄ ነው ሲሉ ዶ/ር ሂርሞን መኮንን ለDW ተናግረዋል። የማህጸን ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት ከ 172 በሚበልጡ ሀገራት ይሰጣል ።

ሀና ደምሴ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ