1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደሞዝ ጭማሪው «ሳይመጣ የሄደ ተስፋ» ወይስ ደጓሚ ?

እሑድ፣ መስከረም 19 2017

ገና ለገና የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግ ነው በሚል በተለይ በመሰረታዊ የፍጆታ ቁሳቁሶች ላይ ተከታታይነት ያለው ጭማሪ እየታየ መሆኑን ሸማቾች ይናገራሉ ። ይህ ደግሞ የሰራተኛውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም ይደግፋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የደሞዝ ጭማሪ ተስፋ እንዳያመነምን ያሰጋል ።

https://p.dw.com/p/4lCpF
Äthiopien | Geldscheine Währung
ምስል MICHELE SPATARI/AFP

ለመንግስት ሰራተኞች የታሰበው የደሞዝ ጭማሪ ምን ያህል ይደጉማል ?

የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ  በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ ጎኑ የሚገለጽ  የኤኮኖሚ ማሻሻያ ባደረገ ማግስት ለመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑ ተሰምቷል።

ለመንግሥት ሠራተኞች የታሰበው የደሞዝ ጭማሪ

የደሞዝ ጭማሪው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ መምህራን እና የጤና ባለሞያዎችን ጨምሮ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ የመንግስት ሰራተኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

ገና በሂደት ላይ ያለው እና የመጨረሻ ውሳኔ ያላገኘው የደሞዝ ጭማሪ በዝቅተኛ የደሞዝ እርከን ላይ ያሉትን ሰራተኞች ከሶስት መቶ ሰላሳ በመቶ በላይ ጭማሪ እንደሚያስገኝ ሲጠበቅ እስከ ከፍተኛው የደሞዝ እርከን ያሉ ሰራተኞችም እንደደረጃቸው የደሞዝ ጭማሪ እንደሚደረግላቸው ይጠበቃል።

Äthiopien | Geldscheine Währung
አንድ ግለሰብ ባለአንድ መቶ ብር ኖት በቆጠራ ላይ ምስል MICHELE SPATARI/AFP

የደሞዝ ማስተካከያና የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ መጨመር

ነገር ግን በሀገሪቱ የዋጋ ግሽበቱ በአንድ ቀን ውስጥ ልዩነት በሚያሳይበት በአሁኑ ወቅት መንግስት ተግባራዊ ሊያደርገው የተቃረበው የደሞዝ ጭማሪ ምን ያህል የሰራተኛውን ኑሮ ይደጉማል የሚለው ጥያቄ ጎልቶ ይሰማል።

በሌላ በኩል በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያሉ እና የኑሮ ውድነቱ ፈተና የሆነባቸው  የመንግስት የልማት ድርጅቶች እና የግል ድርጅት ሰራተኞች ጉዳይን በተመለከተ መፍትሄ ስለመቀመጡ ለጊዜው የተባለ ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም የገንዘብ ድርጅት በቀረበ ብድር  ተግባራዊ ያደረገው የኤኮኖሚ ማሻሻያ በያዝነው ዓመት  የጥር  ገደማ «የዋጋ ግሽበቱ ከ30 እስከ 35 በመቶ ሊደርስ እንደሚችል » ተተንብይዋል።

የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ

በተጨማሪ ገና ለገና የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግ ነው በሚል በተለይ በመሰረታዊ የፍጆታ ቁሳቁሶች ላይ ተከታታይነት ያለው ጭማሪ እየታየ መሆኑን ሸማቾች ይናገራሉ ። ይህ ደግሞ የሰራተኛውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም ይደግፋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የደሞዝ ጭማሪ ተስፋ እንዳያመነምን ያሰጋል ።

የደሞዝ ጭማሪ ያስከተለው ስጋት 

መንግስት በተለይ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰራተኞቹን ኑሮ ለመደጎም የደሞዝ ጭማሪ ሲያደርግ የጎንዮሽ ተግዳሮቶችን እንዴት ይቆጣጠራል የሚለው ጥያቄ መነሳቱም አይቀርም ።

«የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ሳይመጣ የሄደ ተስፋ ወይስ ደጓሚ ?» የእንወያይ ዝግጅታችን የዉይይት ርዕስ ነው ።

ታምራት ዲንሳ