1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች የጡረታ ክፍያ መጠን ጥያቄ

ማክሰኞ፣ ጥር 10 2014

የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ ክፍያ ጭማሪ በየ ሦስት ዐመት ወይም ከዚያ በታች በሆነ ጊዜ እንዲደረግ ተጠየቀ። በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመንግስትና የግል ድርጅቶች ሰራተኞችን ጡረታ ለመቆጣጠር በቀረቡ ሁለት ረቂቅ አዋጆች ዙሪያ ዛሬ በምክር ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይቷል።

https://p.dw.com/p/45hLz
Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed Parlament
ምስል Yohannes Gebireegziabher/DW

የጡረታ ባለመብቶች የላቀ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያለመ ረቂቅ

የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ ክፍያ ጭማሪ በየ ሦስት ዐመት ወይም ከዚያ በታች በሆነ ጊዜ እንዲደረግ ተጠየቀ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመንግስትና የግል ድርጅቶች ሰራተኞችን ጡረታ ለመቆጣጠር በቀረቡ ሁለት ረቂቅ አዋጆች ዙሪያ ዛሬ በምክር ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይቷል። አዲስ የቀረቡት ረቂቅ ዐዋጆች በአንድ በኩል ለአሥር ዐመታት ያገለገሉና የጡረታ ክፍያ መጠኑ አሁን ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ያልተጣጣመ መሆኑ ፣ በሌላ በኩል በባንኮች የሚንቀሳቀሰው የጡረታ ገንዘብ ትርፍ የሚያስገኝበት አሠራር ተዘርግቶ የጡረታ ባለመብቶች የላቀ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማሰብ የቀረቡ ናቸው ተብሏል።

በውይይቱ ጡረተኞች በጤና መድን ሽፋን ውስጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑም ተጠይቋል።

በኢትዮጵያ የጡረታ መውጫ ዕድሜ 60 ዐመት ሲሆን 25 ዐመታትን በመንግሥት ሥራ ያገለገሉ ሠራተኛች በ55 ዐመታቸው የጡረታ መብታቸውን አስከብረው ከሥራ እንዲሰናበቱም ሕግ ይፈቅዳል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ