1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመስቀል በዓል «ጋሪ ወሮ» በሺናሻ ብሔረሰብ

ሰኞ፣ መስከረም 17 2014

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመስቀል በዓል በተለያዩ ብሔረሰቦች ዘንድ በተለያዩ ስነስረዓቶች ተከብሮ ውሏል። የመስቀል በዓል«ጋሪ ወሮ» በተለይ በሺናሻ ብሔረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ እንደሚሰጠው ይነገራል። የብሔሩ አባላት ዕለቱን ከመስቀል በዓልነቱ ባሻገር እንደ አዲስ ዓመታቸውን የሚቀበሉበት ዕለት እንደመሆኑ መጠን የተለየ ድምቀት አለው።

https://p.dw.com/p/40vAZ
Äthiopien Volk der Shinasha / Bworo | Yehuala Abebe
ምስል Negassa Desalegen/DW

የመስቀል በዓል በሺናሻ ብሔረሰብ ዘንድ በድምቀት ተከብሮ ዋለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመስቀል በዓል በተለያዩ ብሔረሰቦች ዘንድ በተለያዩ ስነስረዓቶች ተከብሮ ውሏል። የመስቀል በዓል«ጋሪ ወሮ» በተለይ በሺናሻ ብሔረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ እንደሚሰጠው ይነገራል። የብሔሩ አባላት ዕለቱን ከመስቀል በዓልነቱ ባሻገር እንደ አዲስ ዓመታቸውን የሚቀበሉበት ዕለት እንደመሆኑ መጠን የተለየ ድምቀት አለው። ከኮሮና ወረርሽኝ በኋላ ለወትሮ የተለመደው በዓሉን በአደባባይ ማክበር ቆሞ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ግን ዳግም በጋራ ማክበር መቻላቸውን የብሔሩ አባላት ይናገራሉ። 

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሠ