1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመሬት መንሸራተት በሲዳማ ክልል

ሰኞ፣ መስከረም 18 2013

በሲዳማ ክልል አርቤጎና ወረዳ በደረሰ የመሬት መናድ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የወረዳው ባለስልጣናት አስታወቁ። ባለሥልጣናቱ ዛሬ ለዶቼ ቬለ ( DW ) እንዳስታወቁት አደጋው ትናንት ቀትር ላይ የደረሰው በወረዳው ሚጢቾ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው።

https://p.dw.com/p/3j7vm
Äthiopien Erdrutsch in Sidama Region
ምስል Arbegona Woreda Government Communication Affairs Office

«ሕይወት ጠፍቷል፣ንብረት ወድሟል»

በሲዳማ ክልል አርቤጎና ወረዳ በደረሰ የመሬት መናድ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የወረዳው ባለስልጣናት አስታወቁ። ባለሥልጣናቱ ዛሬ ለዶቼ ቬለ ( DW ) እንዳስታወቁት አደጋው ትናንት ቀትር ላይ የደረሰው በወረዳው ሚጢቾ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው። በአሁኑ ወቅት እየጣለ ከሚገኘው ዝናብ ጋር ተከትሎ በቀጣይ ተመሳሳይ ጉዳቶች ሊከሰቱ ይችላል የሚል ስጋት ማሳደሩን የሚናገሩ የወረዳው ባለሥልጣናት በተለይ በከፍታማ አካባቢ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲሉም አሳስበዋል ። ከሐዋሳ ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዝርዝሩን ልኮልናል።   

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ