1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሃሮማያ ሐይቅ ነብስ ከዘራ በኋላ ጥቅም መስጠት እንዲችል ምን ታሰበ?

ቅዳሜ፣ ኅዳር 24 2015

በገፀ ምድር የውሀ ሀብት እምብዛም ባልታደሉት የምስራቅ ሀገሪቱ አካባቢዎች የሀረማያ ሀይቅ ብርቅዬው ሀብት ነው። የውሀው መጠን ቀስ በቀስ ከመቀነስ አልፎ ሙሉ በሙሉ ከገፀ ምድር ድርቆ እስከጠፋበት ጊዜ ድረስ ዘርፈ ብዙ ግልጋሎቶችን ሰጥቷል።

https://p.dw.com/p/4KRCH
Äthiopien Haromaya-See
ምስል Messay Teklu/DW

የሃሮማያ ሐይቅ ለስራ ፈላጊዎች አዲስ ተስፋ መሆኑ እየታየ ነው

ከአስራ ሰባት አመታት በኃላ ዳግም መመለስ የቻለው የሀረማያ ሀይቅ አሁን ያለበት ደረጃ ጥሩ ቢሆንም ስጋቶች ግን መኖራቸውን ዲ/ር ይስሀቅ ጠቅሰዋል።

አቶ ረመዳን አሊ ሀጂ በወቅቱ በሀይቁ መድረቅ በእጅጉ ካዘኑና በክስተቱም በወቅቱ አገልግሎት ይሰጡባቸው የነበሩ አነስተኛ ጀልባዎች ስራ በማቆማቸው ቀጥተኛ ተጎጂ ነበር። ዛሬ ላይ በጣም ደስታ እንደተሰማው የሚናገረው አቶ ረመዳን ዳግም ጀልባዎችን ይዞ ወደ ስራ ገብቷል። እሱ ብቻም ሳይሆን በርካቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግሯል።

ከሀይቁ የሚገኘውን የአሳ ምርት በመጥበስ ወደ ንግድ ስራ የተመለሱት ወ/ሮ ማውርዲ መሀነድ ተመሳሳይ አስተያየት ሰተዋል።

ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በሀይቁ ዙርያ ለሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ከሁለት መቶ ሃምሳ ሚሊየን ብር በላይ የሚፈጅ ፕሮጀክት ቀርፃ ወደ ተግባር ለማስገባት መዘጋጀቱን ለማወቅ ተችሏል።

ሀረማያ ሀይቅ 

Äthiopien Haromaya-See
በሐሮማያ ሐይቅ ዓሳ በማስገርስራ ላይ የተሰማሩ ምስል Messay Teklu/DW

በገፀ ምድር የውሀ ሀብት እምብዛም ባልታደሉት የምስራቅ ሀገሪቱ አካባቢዎች የሀረማያ ሀይቅ ብርቅዬው ሀብት ነው። የውሀው መጠን ቀስ በቀስ ከመቀነስ አልፎ ሙሉ በሙሉ ከገፀ ምድር ድርቆ እስከጠፋበት ጊዜ ድረስ ዘርፈ ብዙ ግልጋሎቶችን ሰጥቷል።

ዛሬ ላይ በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የሚገኙት ዶ/ር ይስሀቅ በልጅነታቸው ስለተዝናኑበት የሀረማያ ሀይቅ ትዝታ ካላቸው የአካባቢው ተወላጆች አንዱ ናቸው " የዛሬ አርባ አመታት በፊት ህፃን ሆኜ እዚህ አካባቢ መጥቻለሁ። ከአባቴ ጋር እዚህ ሀይቅ ላይ ሄደናል ሁለት ሶስተኛ ክፍል ሆኜ ማለት ነው። ያኔ የነበረው ገፅታ ቆንጆ ነው።" ሲሉ ወደ ኃላ መለስ ብለው የሚያስታውሱትን ሀረማያ ሀይቅ እጅግ ውብነት ይገልፁታል።

የብዙዎችን ስሜት የሰበረው የሀይቁ መድረቅን ተከትሎ ሀይቁ የነበረበት ቦታ ወደ እርሻነት ፤ የተሽከርካሪ መንቀሳቀሻ ሆኖ እንደነበርም አንስተዋል። የሀይቁ መመለስ በጣም አስደሳች ነው የሚሉት ዶ/ር ይስሀቅ ህብረተሰቡንም ተፈጥሮአዊው የሀይቁ ሀብት ካልተጠበቀ የሚጠፋ በሚደረግለት እንክብካቤም የሚመለስ መሆኑን አስተምሯል ብለዋል።

በሀይቁ ዳርቻ ተወልደው ያደጉት አቶ ረመዳንም በርካቶች የሚዝናኑበት ፣ ጥንዶች የሰርግ ፎቶግራፍ የሚነሱበት ፣ ዓሳ በሚሰገርበት ሀረማያ ሀይቅ በወቅቱ በነበሯቸው አራት ያህል አነስተኛ የእንጨት ጀልባዎች ኑሯቸውን አቆራኝተው የነበሩበትን ሀረማያ ሀይቅ አይረሱትም ።

Äthiopien Haromaya-See
የሀሮማያ ሐይቅምስል Messay Teklu/DW

በሀይቁ መድረቅ እኔም ቤተሰቦቼም በእጅ አዝነን ነበር የሚሉት አቶ ረመዳን" በወቅቱ የነበሩንን አራት ጀልባዎች በመጥረቢያ ሰባብረን ኑሮን ለመግፋት ወደ ሌላ አካባቢ ሄድን" ሲሉ ክፉውን ግዜ ያነሳሉ ።

ከአስራ ሰባት አመታት በኃላ ውሀው በመመለሱ በእጅጉ ከተደሰቱ ሰዎችም ቀዳሚ የሆኑት አቶ ረመዳን ዳግም የእንጨት ጀልባዎችን አዘጋጅተው ወደ ስራ ተመልሰዋል።

በሀይቁ ዳርቻ የአሳ ምግቦችን አዘጋጅተው ወደ መሸጥ ስራ የገቡት ወ/ሮ ማውርዲ መሀመድ በውሀው መመለስ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እና ሀረማያ ሀይቅ

በእድሜ አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ አጠገብ የሚገኘው ሀይቅ መድረቅ በወቅቱ ከተለያዩ አካላት የተለያዩ ጥያቄያዊ ይዘት የነበራቸው አስተያየቶችን አስነስቷል።

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይስሀቅ ዩሱፍ "  የሀይቁን ህልውና መመለስ ግዴታችን ነው ብለን ነው የምናየው ምክንያቱም ዩኒቨርሲቲ ሁልጊዜም የህብረተሰቡን ችግር ነፍትታ አለበት " ብለዋል ። 

Äthiopien Haromaya-See
የሐሮማያ ሐይቅ የጀልባ አገልግሎትምስል Messay Teklu/DW

በተለይ በሀይቁ ዙርያ ባሉ አካባቢዎች በየዓመቱ ከአራት መቶ ሺህ በላይ የዛፍ ችግኞችን ከመትከል ጀምሮ  የተከናወኑ ሌሎች የተፋሰስ ልማት ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል።

የሀይቁን ህልውና ለማስቀጠልም ከህብረተሰቡ እና ከአካባቢው መስተዳድር ጋር የተለያዩ ስራዎች እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ወደ ሀይቁ የሚገባ ደለልን መከላከል እና ከሀይቁ ለመስኖ አገልግሎት የሚሳብ የውሀ መጠን ላይ መፍትሄዎች ካልተቀመጡ ህልውናው ዳግም ችግር ውስጥ ሊወድቅ እንደሚችል የሚያስረዱት ዶ/ር ይስቅሀ ዩኒቨርሲቲው በዚህ ረገድም መፍትሄዎችን ለማስቀመጥ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

Äthiopien Haromaya-See
ወጣቶች በሐሮማያ ሐይቅ ላይ ሲዝናኑምስል Messay Teklu/DW

ከዚህ ጎን ለጎን የሀይቁን ዙርያ ለማልማት የሚስችል ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ ፕሮጀክት ቀርፃ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅት መደረጉን እና ይሄንኑ ለመደገፍ ፍላጎቱ ካላቸው አካላት ጋር ለመስራት ቁርጥኛ መሆናቸውን አስረድተዋል።

መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ