1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን የኳስ «ንጉሠ-ነገሥት» የ78 ዓመቱ ፍራንስ ቤከን ባወር አረፈ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 29 2016

በጀርመን እግር ኳስ ታሪክ ስመ ጥር ዝና ካተረፉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው የ78 ዓመቱ ፍራንስ ቤከን ባወር ትናንት ማረፉ ተገለጸ ። የጀርመን እግር ኳስ ማኅበር ዕውቁ የኳስ ሰው ማረፉን ዛሬ ዐስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/4b04r
BG Franz Beckenbauer | deutscher Fußballspieler
ምስል SvenSimon/picture alliance

በጀርመን እግር ኳስ ታሪክ ስመ ጥር ዝና ካተረፉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው የ78 ዓመቱ ፍራንስ ቤከን ባወር ትናንት ማረፉ ተገለጸ ። የጀርመን እግር ኳስ ማኅበር ዕውቁ የኳስ ሰው ማረፉን ዛሬ ዐስታውቋል ። ቤንከንባወር በጀርመን የእግር ኳስ ታሪክ በተጨዋችነትም ሆነ በአሰልጣኝነት ዘመን የዓለም ዋንጫ ካነሱ ሦስት ጀርመናውያን መካከል አንዱ ነው ። ፍራንስ ቤከን ባወር ያረፈው ከጤና ችግር ጋ በተያያዘ መሆኑም ተዘግቧል ።  የታኅሣሥ 29 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በጀርመን የስፖርት አፍቃሪያን ዘንድም «ንጉሠ-ነገሥት» በሚል ቅጽል ስም ይታወቃል ። ለጀርመን ስፖርት ታላቅ አስተዋጽዖ ያበረከተው ይህ የስፖርት ሰው በዕድሜዎቹ መገባደጃ ላይ ግን ጀርመን እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2006 የዓለም ዋንጫን እንድታዘጋጅ ለማስቻል በተፈጸመ ቅሌት ውስጥም ስሙ ይነሳል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ