1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ስለ ሴቶች መብት ያዘጋጀችው ጽሑፍ ያሸለማት ታዳጊ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 8 2016

ሩት ሳሙኤል አሸናፊ የሆነችበት ጽሑፍ "ሴቶች ሥልጣን ላይ ቢወጡ ዓለማችን ምን ትመስል ነበረ" የሚል ርእስ ያለው ነው። ታዳጊዋ ይህንን ጽሑፍ ለማዘጋጀት እህቷ ሥራ ለመቀጠር ጥረት በምታደርግበት ወቅት ሴትነቷን መሠረት በማድረግ የደረሰባት ያልተገባ የጾታ መድልዎ ላይ መሆኑን ገልጻለች።

https://p.dw.com/p/4jROO

በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ እና የብሪቲሽ ካውንስል አንድ የጽሑፍ ውድድር አዘጋጅተው ነበር። በዚህ የሥነ ጽሑፍ ውድድር ከ14 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ300 በላይ ተማሪዎች ያሸንፍልናል ያሉትን ጽሑፍ ለውድድር ይዘው የቀረቡ ሲሆን አዲስ አበባ የሚገኘውና ሴቶች ብቻ የሚማሩበት ናዝሬት ትምህርት ቤት ውስጥ የ11 ክፍል ተማሪ የሆነችው ሩት ሳሙኤል የሴቶች መብትን በሚመለከት ባሰናዳችው ጽሑፍ አሸናፊ ሆናለች።

ታዳጊዋ ይህንን ውድድር በማሸነፏ "Ambassador for a day 2024" በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ የ2024 የአንድ ቀን አምባሳደር የሚለውን ሽልማት ለማግኘት ችላለች።

ይህንን ተከትሎ በBritish Council ውስጥ የሚከናወኑ ሥራዎችን ለመጎብኘት፣ ከእንግሊዝ አምባሳደር በኢትዮጵያ ጋር በኤምባሲው የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንዲሁም ከትውልደ ኢትዮጵያዊው እውቅ ገጣሚ ለምን ሲሳይ ጋር የመወያየት እድል አግኝታለች።

#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ፡ ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ፡ ሰለሞን ሙጬ