1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ያለ እድሜ የሚከሰት እርግዝና

ረቡዕ፣ ነሐሴ 18 2014

ወጣት ሴት ልጆች ካሰቡበት ለመድረስ በሚያደርጉት ጥረት እክል ከሚሆኑ ጉዳዮች አንዱ ያለ እድሜ የሚከሰት እርግዝና ነው። አሁን አሁን የችግሩ ስፋት የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳዩቱ መረጃዎች ለጉዳዩ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት የሚያመላክቱ ናቸው። ለችግሩ መከሰት የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ወጣቶችን ለፃታዊ መሳሳብ የሚዳርጉ ዝግጅቶች አስተዋፅአቸው የጎላ ነው።

https://p.dw.com/p/4Fyi7

ለዝግጅታችን አስተያየት የሰጡት መምህር አሸቱ ፈይሳ በትምህርት ቤቶች የሚዘጋጁ አንዳንድ ዝግጅቶች ጠቃሚ ጎን ቢኖራቸውም ወጣቶቹን "ለፆታ መሳሳብ ይዳርጋቸዋል" ፤ ይሄም ወጣት ሴት ልጆችን ያለዕድሜ ለሚከሰት እርግዝና እንዲጋለጡ ያደርጋል ብለዋል። 

በትምህርት ቤቶች ስርዓተ ፆታን በሚመለከት ትምህርት ቢሰጥም ትምህርቱ ጠበቅ ባለና ተማሪው ከመሰል ችግሮች እንዴት ራስን መጠበቅ እንደሚችሉ ጠበቅ ያለ እውቀት እና ክህሎት ማስጨበጥ ላይ ድክመት ይታያል የሚሉት መምህር እሸቱ ይህም ለችግሩ መከሰት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

ማንኛውም ወጣት ለአካለ መጠን በደረሰ ጊዜ የሚሰማው የፃታ ፍላጎት መነሳሳት ተፈጥሯዊ ነው ያሉት መምህር እሸቱ ይሁን እንጂ ይህንን ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ የመጣን የፃታ ፍላጎት መነሳሳት ለመግታት አዕምሮን  መጠቀም ይገባል የሚል ምክረ ሀሳብ አንስተዋል።

በአጠቃላይ በወጣትነት እድሜ ምዕራፍ የሚገጥምን መሰል ችግር ለመከላከል የራሳቸው የወጣቶች ፣ ወላጆች ፣ ትምህርት ቤቶችና ሌሎች አካላት የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል የሚለው የብዙዎች የጋራ ሀሳብ ነው።

በድሬደዋ አስተዳደር  ጤና ቢሮ የጤና ማበልፀግ ኬዝ ቲም አስተባባሪ ሲስተር መሰሉ አጥናፌ ለዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊዲያ መለስ እንዳብራሩት እድሜያቸው ድሬደዋ ውስጥ ፅንስ የሚያጨናግፉት መካከል  14 በመቶ ያህሉ እድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ሴቶች ናቸው።  

ዘገባ: ሊዲያ መለስ
ቪዲዮ: መሳይ ተክሉ