1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የዓሳ ቁርጥ አዘጋጆቹ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 5 2015

ዱቢቴ ወየሳ እና ውቤ መንታሞ በሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ላይ የዓሳ ቁርጥ በማዘጋጀትና በመሸጥ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በኑሮ ይደግፋሉ ፡፡ የ15 ዓመት አዳጊ የሆኑት ዱቢቴ እና ውቤ የዓሳ ቁርጥ መበለትና ማዘጋጀት ከእናቶቻቸው መልመዳቸውን ይናገራሉ ፡፡

https://p.dw.com/p/4KuKK

አሁን ላይ በቀን በዚሁ ሥራ በማሳለፍ በማታው ደግሞ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡ ወደፊት ትልቅ ደረጃ ላይ የመድረስ ህልም እንዳላቸው የሚናገሩት አዳጊዎቹ ዱቢቴ መምህር ውቤ ደግሞ ሐኪም የመሆን ፍላጎት እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘጋቢ ፡ ሊሻን ዳኜ
ቪዲዮ ፡ ሸዋንግዛው ወጋየሁ