1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የክለብ ተጫዋቾቹ ታዳጊዎች

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 10 2015

የ17 ዓመት ታዳጊ የሆኑት ብሌን ሲሳይ እና መሠረት ፈረደ የኢትዮ ኤሌክትሪክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች ናቸው ፡፡ ከልጅነታቸው ጀምሮ የነበራቸው የእግር ኳስ ፍቅር አሁን ላይ የክለብ ተጫዋች ለመሆን አብቅቷቸዋል።

https://p.dw.com/p/4LAgr

ብሌን እና መሠረት እዚህ ለመድረስ ካጋጠሟቸው ችግሮች መካከል ዋነኛው የማህበረሰቡ የተዛባ አመለካከት ነው ይላሉ ፡፡ በእግር ኳስ ተጫዋችነት ለመሳተፍ ባደረጉት ጥረት ሴት መሆናቸው ብቻውን ፈተናውን ከባድ እንዳደረገባቸውም አዳጊዎቹ ገልጸዋል፡፡  በተለይም ከአንዳንድ ሰዎች በጎ ያልሆኑ አስተያየቶች ይሰነዘሩባት እንደነበር የምትናገረው ብሌን ይህ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ሠርታ ለማሳየት ይበልጥ እንዳነሳሳት ትናገራለች ፡፡ መሠረት ደግሞ ከአሰልጣኝ እና ከሌሎች ተጫዋቾች ያገኘችው ምክር ቤተሰቦቿን እና ማህበረሰቡን ለማሳመን እንደረዳት ትናገራለች። የቡድናቸው አሰልጣኝ የሆኑት መሠረት ማኔ« የልጆቹ ህልም እንዲሳካ የክለብ ወይም የአሰልጣኝ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የህብረተሰብ፣ የቤተሰብ እና የመንግሥትም ኃላፊነት ነው ይላሉ። #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘጋቢ ፡ ሊሻን ዳኜ 
ቪዲዮ ፡ ሸዋንግዛው ወጋየሁ