1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የሴት ልጅ ግርዛት ትግል

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 5 2013

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም ድረስ የሴት ልጅ ግርዛት በድብቅ ይፈፀማል። በድሬደዋ ከተማ በሚገኝ አንድ ማዕከል የሴቶችና ህፃናት ጥቃት የወንጀል ምርመራ ማስተባበርያ ኃላፊ የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ጥላሁን ቸርነት ለዝግጅታችን እንደገለፁት በቅርቡ ወላጆቿ አስገርዘዋት እና ለሳምንት ያህል ቤት ውስጥ አቆይተዋት ልጅቷ ክፉኛ በመታመሟ የተነሳ ወደ ሀኪም ቤት ስለወሰዷት ድርጊቱ ሊጋለጥ ችሏል።

https://p.dw.com/p/3rvox

በድሬደዋ ከተማ በሚገኝ አንድ የህፃናት መብት ጥበቃ ክበብ አባል የሆኑት ዮሐንስ ሀብታሙ እና ቅድስት አያሌው ለምሳሌ ይህንን ጎጂ ልማድ ለማስቆም የምክር አገልግሎት በመስጠት የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ ይገኛሉ። የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊዲያ መለስ ድርጊቱ የተፈፀመባቸው ሴቶችን በአካል አግኝታ ለማነጋገር ባትችልም የሴት ልጅ ግርዛት ስለሚያስከትለው ጉዳት የሴቶች፣ ወጣቶች እና የኤች አይ ቪ ባለሙያም አነጋግራ በዛሬው የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዝግጅት ትጠብቃችኋለች።
ዘገባ: ሊዲያ መለስ
ቪዲዮ: መሳይ ተክሉ