1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የሞዴል ዩናይትድ ኔሽን ተሸላሚ

ዓርብ፣ ነሐሴ 13 2014

የ17 ዓመት ታዳጊ ሶፊያ ጀማል የ12ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ባለብዙ ተስጥኦም ናት፡፡ ሶፊያ በቅርቡ በቱርክ ኢስታንቡል በተዘጋጀው በተባበሩት መንግስታት ታዳጊዎች ውጤታማ የአመራር ክህሎትና ዲፕሎማትነት የሚለማመዱበት በሞዴል ዩናይትድ ኔሽን (MUN) ፕሮግራም ተሸልማ አምባሳደር ተሰኝታለች፡፡

https://p.dw.com/p/4FmRr

ታዳጊዋ በስዕል ችሎታዋም የተካነች ነች፡፡ ለባህላዊና ዘመናዊ ፋሽን የሚውሉ የተለያዩ አልባሳት ዲዛይን የማኖር ክህሎት አላት፡፡ ሶፊያ ከስዕል ችሎታዋም በተጨማሪ በኮምፒዩተር ኮዲንግ ስራ ድረገፅ  በማበልጸግ ላይ ስትሆን ይህንንም ኢትዮጵያ የምትታወቅባቸው የባህላዊ መድኃኒቶችን ከነጥቅማቸው ማስተዋወቂያ ለማዋል ታልማለች፡፡ ከባለ ብርሁ ራዕይ ታዳጊ ሶፊያ ጀማል ጋር የአዲስ አበባ የዶቼ ቬለ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች አዘጋጅ ሱመያ ሳሙኤል ለቃለ ምልልስ ተቀምጣ ነበር፡፡ 
ዘገባ: ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ: ሥዩም ጌቱ