1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከጎዳና እና ሱስ የተላቀቀችው ሐና

ረቡዕ፣ መስከረም 4 2015

በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆነችው የ18 ዓመቷ ታዳጊ ወጣት ሐና ታደለ ላለፉት ሦስት ዓመታት ኑሯዋን በጎዳና አድርጋ መቆየቷን ትናገራለች ፡፡ ‹‹ የጎዳና ሕይወት በተለይ ለሴቶች በጣም አስቸጋሪ ነው ›› የምትለው ሐና ቦታው ጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ ለተለያዩ ሱሶች እንደሚያጋልጥ ካሳለፈችው ህይወት በመነሳት ትገልጻለች ፡፡ 

https://p.dw.com/p/4Gq3A

በአንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት አማካኝነት ባገኘችው የሥነ ልቦና ድጋፍ አሁን ላይ ከተለያዩ ሱሶች መላቀቋን የምትናገረው ሐና ‹‹ ቀጣይ ሕይወቴን የተሳካ ለማድረግም በባጃች ታክሲ አሽከርካሪነት ሙያ እየሠለጠንኩ እገኛለሁ ›› ብላለች ፡፡ ሐናን ጨምሮ ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ አዳጊ ወጣቶችን እየደገፈ የሚገኘው እና «ሴንተር ኦፍ ኮንሰርን» በተባለው በጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ በሥነ ልቦና ባለሙያነት እያገለገሉ የሚገኙት ተስፉ ዋርጃ በበኩላቸው በጎዳና ላይ የሚገኙ አዳጊዎችና ወጣቶች ከአካላዊ ጉዳት እስከ ሞት የሚደርሱ ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው ይገኛሉ ይላሉ፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute


ዘገባ ፦ ሊሻን ዳኜ
ቪዲዮ ፦ ሸዋንግዛው ወጋየሁ