1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች : እግር ኳስ ተጫዋቿ ሶፋኒት ተፈራ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 12 2013

እግር ኳስ የወንዶች ጨዋታ ብቻ አይደለም ። በአሁኑ ጊዜ በርካታ እንደ ሶፋኒት ተፈራ ያሉ አዳጊ ሴቶች የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎቻቸውን ወደ ሙያ ለመቀየር እድል አግኝተዋል። «ሌሎች ሴቶች ስኬታማ ሆነው አሳይተውናል። እኛም በእነሱ ስር ነው የምናልፈው» ትላለች ብዙ ፈተና እንዳልገጠማት የምትናገረው ሶፋኒት። በሴቶች ክለቦች ከመጫወቷ በፊት ግን ከወንድሞቿ እና በሰፈሯ ካሉ ወንድ ልጆች ጋር ብቻ ነበር እግር ኳስ የመጫወት አድል የነበራት። የ«ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች» #GirlZOffMute ዘጋቢ አምራን ወንዶሰን፤ ሶፋኒትን ልምምድ ቦታ አግኝታት ቆይታ አድርገዋል። ዘገባ : አምራን ወንዶሰን ካሜራ : ዮሐንስ ገብረ እግዚያብሔር

https://p.dw.com/p/3n0C4