1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 26 2014

በሀዋሳ ከተማ ሰሞኑን በተካሄደው አገር አቀፍ የዌልቸር (የተሽከርካሪ ወንበር) ቅርጫት ኳስ ውድድር ከተሳተፉት ወጣት አካል ጉዳተኞች መካከል የ19 ዓመቷ ሠዓዳ አብደላ አንዷ ናት።

https://p.dw.com/p/4Ao9b

የደቡብ ክልል የቅርጫት ኳስ ቡድንን በመወከል ከጉራጌ ዞን ወልቂጤ የመጣችው ሠዓዳ በውድድሩ ያሳየችው እንቅስቃሴ የብዙዎችን ትኩረት እንድታገኝ አድርጓታል፡፡ አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል አካል ጉዳተኞች በስፖርት ዘርፍ ይሳተፋሉ የሚል ግምት እንደሌለው የምትናገረው ሠዓዳ « ስፖርቱ ለእኔ ብዙም አልከበደኝም» ትላለች ፡፡ በቴክኒክ ሙያ ተመርቃ ስራ ያላገኘችው ሠዓዳ በአሁኑ ሰዓት ትኩረቷን ስፖርቱ ላይ አድርጋለች።

ዘጋቢ ፡ ሊሻን ዳኜ
ቪዲዮ ፡ ሸዋንግዛው ወጋየሁ