1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: አልባሳቱና ታሪኮቻቸው

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 4 2014

እውን አለባበስ ለጾታዊ ጥቃት ምክንያት ሊሆን ይችላልን ? «ጾታዊ ጥቃት መነሻው የግለሰቦች የተዛባ ሥነ ልቦናዊ አስተሳሰብና አመለካከት እንጂ ከአለባበስ ጋር ተዛማችነት የለውም» ይላሉ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአንቺው ንቅናቄ በሚል የክበብ መጠሪያ የተሰባሰቡ ተማሪዎች ። 

https://p.dw.com/p/449uQ

በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ጥቃት በተፈጸመባቸው ወቅት ለብሰውት የነበረውን አልባሳት በማሰባሰብ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ባዘጋጁት እውደ ርዕይ ላይ ለእይታ ማቅርባቸውን የክበቡ የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ተማሪ እጸገነት መልካሙ ገልጻለች ። 


ዘገባ: ሊሻን ዳኜ 
ካሜራ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ