1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ሴት ስኬተሮች

ሰኞ፣ ነሐሴ 23 2014

ስኬት ቦርድ መንዳት ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙም የተለመደ አይደለም። በተለይ ደግሞ ሴት ኢትዮጵያውያን ሲነዱ አይስተዋልም። ይሁንና ከቅርብ ዓመታት አንስቶ ቢያንስ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ይህንን የሚነዱ ወጣቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መጥተዋል።

https://p.dw.com/p/4GAee

በአዲስ አበባ መካኒሳ አካባቢ በቡድን ተሰባስበው ስኬት ቦርድን የሚለማመዱ ሴት ታዳጊዎች ለዶይቼ ቬለ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሱመያ ሳሙኤል እንደገለፁላት ስፖርቱ ደፋር አድርጓቸዋል፣ በራስ መተማመናቸውም ጨምሯል። የሴት ስኬትቦርዲንግ መስራች ህሊና ሰለሞን «ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት 13 ሴት አባላት እና 10 ስኬት ቦርዶች አሉት» ትላለች። ሴቶቹ ስኬት ቦርድ የሚነዱት ለጊዜ ማሳለፊያ ወይም እዛ ላይ ሆኖ ፎቶ ለመነሳት ሳይሆን ወደፊት ስፖርቱን ሙያቸው አድርገው ሀገራቸውን ማስጠራት ስለሚፈልጉም እንደሆነ ነግረውናል። #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ፡ ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ፡ ሥዩም ጌቱ (DW) ከአዲስ አበባ