1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉይይት፤ የሰላማዊው ትግል ጥሪ አንደምታ በፖለቲካው ዘርፍ ላይ

እሑድ፣ ሐምሌ 1 2010

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባለፈው መጋቢት 24፣ 2010 ዓም ስልጣን ከያዙ ወዲህ ሰፊ የለውጥ ርምጃዎች አነቃቅተዋል። ከአጠቃላዩ ብሔራዊ እርቀ ሰላም ጥሪ ጎን፣ የመንግሥት ይዞታ የነበሩ የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለግሉ ይዞት ክፍት ማድረግ፣ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት የመሳሰሉ ይጠቀሳሉ።  

https://p.dw.com/p/30xx0
Addis Abeba, Äthiopien, Äthiopischer Premierminister Abiy Ahmed im Parlament
ምስል DW/Y.Geberegziabher

ዉይይት፤ የሰላማዊው ትግል ጥሪ አንደምታ በፖለቲካው ዘርፍ ላይ


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባለፈው መጋቢት 24፣ 2010 ዓም ስልጣን ከያዙ ወዲህ ሰፊ የለውጥ ርምጃዎች አነቃቅተዋል። ከአጠቃላዩ ብሔራዊ እርቀ ሰላም ጥሪ ጎን፣ የመንግሥት ይዞታ የነበሩ የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለግሉ ይዞት ክፍት ማድረግ፣ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት የመሳሰሉ ይጠቀሳሉ።  የፖለቲካ ምህዳሩን ለማሻሻል እና ዴሞክራሲን ለማስፋት፣  የራሳቸውን ገዢ ፓርቲ ሳይቀር ለማደስም እየሰሩ እንደሆኑ ይነገራል።  ጠቅላይ ሚንስትሩ ከወሰዷቸው ርምጃዎች መካከል በሀገር እና በውጭ ሀገር ላሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በሰላማዊ ትግሉ እንዲሳተፉ ያቀረቡት ጥሪ ይጠቀሳል። ይህንኑ ጠ/ሚንስትሩ ለተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ ትግል እንዲሳተፉ ያቀረቡትን ጥሪ እና በሀገሪቱ እየታየ ያለውን ለውጥ አዎንታዊ አድርገው የተመለከቱ  በውጭ የሚገኙ አንዳንድ የተቃዋሚ  ቡድኖች፣ የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ጭምር ወደ ሀገር ተመልሰዋል።  በመጀመሪያ ወደ ሀገር የተመለሰው በነአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ፣ ኦዴግ ነው።

Oromo Democratic front (ODF) Logo
ምስል Oromo Democratic front

የትጥቅ ትግል ያካሂዱ የነበሩ በብርጋዴየር ጄነራል  ኃይሉ ጎንፋ እና በአባ ነጋ ጃራ የሚመራው  የተባበረው የኦሮሞ ነፃነት  ግንባር፣ እንዲሁም፣ በብርጋዴየር ጄነራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሚያ ነጻነት እና አንድነት ግንባር የተሰኘ የኦነግ አንጃ ከተመለሱት መካከል ይገኙባቸዋል። የአርበኖች ግንባር ግንቦት ሰባትም፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ የጀመሩትን የለውጥ ርምጃዎች እንደሚደግፍ ፣ በቀጣይ  የሚወሰዱ ርምጃዎችን በመመልከትም ወደፊት የቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል የትጥቅ ትግሉን በመተው ወደ ሰላማዊው ትግል ሊቀላቀል እንደሚችልም ተናግሯል።   ለብዙ ዓመታት በውጭ የነበሩ የተቃዋሚ ቡድኖች አሁን ወደ ሀገር እየገቡ ያለበትእና  ካለፉት ጥቂት ጊዚያት ወዲህ እየታየ ያለው አዲስ ሁኔታ በሀገሪቱ የፖለቲካ ዘርፍ ላይ፣ በፓርቲዎች የወደፊት አካሄድ ምን ዓይነት ሚና ይኖረዋል? ፓርቲዎችስ እርስበርስ ምን ዓይነት ግንኙነት ይኖራቸዋል። በዚሁ ርዕስ ላይ የተቃዋሚ ፓርቲ ተጠሪ እና የፖለቲካ ተንታኞች ተወያይተውበታል።

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ