1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከጥሎ ማለፍ ጫወታው በፊት የዶርትሙን ከተማ ድባብ ምን ይመስላል?

ቅዳሜ፣ ሰኔ 22 2016

የ17ኛው አውሮጳ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጫወታዎች ዛሬ ምሽት ይጀመራል። 590,000 ነዋሪዎች ያሏት የዶርትሙንድ ከተማ ዛሬ ማታ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ የጀርመን እና የዴንማርክን ጨዋታ ለማስተናገድ ሽር ጉድ እያለች ነው ።

https://p.dw.com/p/4hfUS
Dortmund vor dem EM Spiel Deutschland Dänemark
ምስል Mantegaftot Sileshi /DW

ከጥሎ ማለፍ ጫወታ በፊት በርካታ ደጋፊዎች ዶርትሙንድ ከተማ ደርሰዋል

የ17ኛው አውሮጳ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጫወታዎች ዛሬ ምሽት ይጀመራል። 590,000 ነዋሪዎች ያሏት የዶርትሙንድ ከተማ ዛሬ ማታ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ የጀርመን እና የዴንማርክን ጨዋታ ለማስተናገድ ሽር ጉድ እያለች ነው ።

 

ዶርትሙንድ ከተማ በቡንደስሊጋው ጠንካራ ተፎካካሪ በሆነው በቦሩስያ ዶርትሙንድ የእግር ኳስ ቡድኗ፤ በዩኒቨርሲቲዋ፤ ዘመናትን ባስቆጠረ የኢንዱስትሪ ማዕከልነቷ እና በቢራዋ ትታወቃለች ። ወደ ከተማዋ ከ100ሺ በላይ ደጋፊዎች መጉረፋቸው ተነግሯል።

የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ዶርትሙንድ ከተማ ውስጥ
የ17ኛው አውሮጳ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጫወታዎች ዛሬ ምሽት ይጀመራል። 590,000 ነዋሪዎች ያሏት የዶርትሙንድ ከተማ ዛሬ ማታ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ የጀርመን እና የዴንማርክን ጨዋታ ለማስተናገድ ሽር ጉድ እያለች ነው ።ምስል Mantegaftot Sileshi /DW

 

የ2016 ዓ.ም የአውሮፓ ዋንጫ መክፈቻ እና የጀርመን ድል

በዝህም ምክንያት ፖሊስ የጸጥታ ጥበቃውን ጥብቅ አድርጎታል። የጀርመን ብሄራዊ ቡድን የዙር ማጣራውን በ7 ነጥብ ከምድቡ አንደኛ ሆኖ ነበር ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለው ። የዛሬው ተጋጣሚው የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ በሶስት ነጥብ ከምድቡ ሁለተኛ ሆኖ ነበር ለጥሎ ማለፉ የበቃው።  

የጀርመን እና ዴንማርክ ደጋፊዎች በዶርትሙንድ
በዝህም ምክንያት ፖሊስ የጸጥታ ጥበቃውን ጥብቅ አድርጎታል። የጀርመን ብሄራዊ ቡድን የዙር ማጣራውን በ7 ነጥብ ከምድቡ አንደኛ ሆኖ ነበር ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለው ። የዛሬው ተጋጣሚው የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ በሶስት ነጥብ ከምድቡ ሁለተኛ ሆኖ ነበር ለጥሎ ማለፉ የበቃው።ምስል Mantegaftot Sileshi /DW

ለአውሮጳ እግር ኳስ ጨዋታ ውድድር የጀርመን ቡዱን ዝግጅት

81 ሺህ ተመልካቾች የማስተናገድ አቅም ባለው ሲግናል ኢዱና ፓርክ ስታዲየም ማን አሸንፎ ወደ ሩብ ፍጻሜ ይሻገር ይሆን? ምሽት አራት ሰዓት ላይ የሚጀመረው ጫወታ ይለያል ። የዶቼ ቬለው ማንተጋፍቶት ስለሺ ዶርትሙንድ ተገኝቶ አጠቃላይ የደጋፊውን ድባብ ተመልክቷል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ታምራት ዲንሳ