1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከአላማጣ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ያሰሙት ቅሪታ

ሰኞ፣ ኅዳር 3 2011

ከነሐሴ መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ ከራያ አላማጣ ተፈናቅለው በቆቦ የመጠለያ ካምፖች የሚገኙ ተፈናቃዮች ከመንግስት የሚደረግልን ድጋፍ የለም አሉ፣ ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/387n7
Äthiopien ethnische Minderheit der Gedio
ምስል DW/Shewngizaw Wegayehu Aramdie

ከነሐሴ መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ ከራያ አላማጣ ተፈናቅለው በቆቦ የመጠለያ ካምፖች የሚገኙ ተፈናቃዮች ከመንግስት የሚደረግልን ድጋፍ የለም አሉ፣ ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ገልፀዋል፣ የትግራይ መንግስት ደግሞ ከአማራ ወደ ትግራይ እንጂ ከትግራይ ወደ አማራ የተፈናቀለ ሰው የለም ሲል በቃል በክልሉ ቃል አቀባይ በኩል አስታውቋል፡፡

አቶ አክሊሉ ትክዬ ገደፋው የተፈናቃዮች ተወካይ ናቸው መንግስት ወደ አካባቢው በመጣንንበት ወቅት 59 ኩንታል እህልና ድንኳኖችን ከማቅረብ ውጭ እደረገ ያለው ድጋፍ የለም ብለዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ኃላፊ አቶ አስረስ ባዬ ለቀረበላቸው ትያቄ አቅም በፈቀደ መጠን ድጋፍ ይደረጋል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ተፈናቃዮች ወደቦታችን ብንመለስ ለደህንነታችን እንሰጋለን የሚለውን ስሞታ በተመለከተ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ለ Dw ቃለምልልሥ ሰተዋል። 

ከትግራይ ወደ አማራ ክልል የተፈናቀለ አንድም ሰው እንደሌለ ጠቁመው ይልቁንም ከአማራ ወደ ትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎችን በማረጋጋትና በማቋቋም ስራ መጠመዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በራያ አላማጣ አካባቢ ከማንነት ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ግጭት በትግራይና አማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሰው ሕይወት መጥፋቱና ንብረት መውደሙ የሚታወስ ነው፡፡

 

ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ