1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሞ ፋራህ በ17 አመቱ ሰለሞን ባረጋ ሊፈተን ይችላል

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 6 2009

ኤርትራውያኑ አሮን ክፍሌ እና አወል ሐብቴ አገራቸውን ወክለው በውድድሩ ይካፈላሉ።

https://p.dw.com/p/2i7lQ
Gebergezihabeher Gebermariam Ethiopian Athletics Federation Pressekonferenz London
ምስል DW/H.Tiruneh

ኢትዮጵያውያኑ በለንደን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሞ ፋራህ ይገጥማሉ

ዛሬ ምሽት ኢትዮጵያውያኑ ሙክታር ኢድሪስ፤ዮሚፍ ቀጀልቻ እና ሰለሞን ባረጋ በለንደን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5,000 ሜትር ከሞ ፋራህ ጋር ይገጥማሉ። ከመም ውድድር በዛሬው ምሽት የሚሰናበተው ሞ ፋራህ በ17 አመቱ ሰለሞን ባረጋ ሊፈተን ይችላል ተብሏል። 
ኤርትራውያኑ አሮን ክፍሌ እና አወል ሐብቴ አገራቸውን ወክለው በውድድሩ ይካፈላሉ። ሲሩስ ሩቶ ብቸኛው ኬንያዊ ነው። ውድድሩ ምሽት 4:20 ላይ ይከናወናል፡፡ በለንደኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10,000 ሜትር ያሸነፈው ሞ ፋራህ ኢትዮጵያውያኑን ከሚቀናቀኑት አትሌቶች መካከል ቀዳሚው ነው።

ኃይማኖት ጥሩነህ

እሸቴ በቀለ