1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አቅጣጫዋ

እሑድ፣ ታኅሣሥ 3 2014

የኢትዮጵያ መንግሥትም ኾነ የኢትዮጵያ ጉዳዮችን ይሁነኝ ብለው የሚከታተሉ ሰዎች በተደጋጋሚ እንደሚገልጡት ዩናይትድ ስቴትስ ከምዕራባውያን አጋሮቿ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የምታሳድረው ጫና ልኩን ያለፈ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነትም የሚገዳደር ነው። የኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በአሁኑ ወቅት ምን ይመስላል? ውይይት።

https://p.dw.com/p/447KX
Äthiopiens Premierminister Abiy Ahmed, Eritreas Präsident Isaias Afwerki und Somalias Präsident Mohamed Abdullahi Mohamed
ምስል Eduardo Soteras/AFP/Getty Images

ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲው ምን መልክ አለው?

ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያ ከምዕራቡ ዓለም ሃገራት ጋር ያላት ግንኙነት መልኩን ቀይሯል። ኢትዮጵያ በዋናነት ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የገባችው ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ከምንጊዜውም በላይ እየጎላ መጥቷል። የኢትዮጵያ መንግሥትም ኾነ የኢትዮጵያ ጉዳዮችን ይኹነኝ ብለው በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች በተደጋጋሚ እንደሚገልጡት ዩናይትድ ስቴትስ ከምዕራባውያን አጋሮቿ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የምታሳድረው ጫና ልኩን ያለፈ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነትም የሚገዳደር ነው።

በአንጻሩ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ያላቸው ቻይና እና ሩስያን ጨምሮ አንዳንድ ሃገራት ድጋፋቸውን ለኢትዮጵያ ሲያንጸባርቁ ይስተዋላል። ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያን የጎበኙት የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ማንኛውንም ጣልቃ ገብነት ሀገራቸው እንደምትቃወም ዐስታውቀዋል። ለኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ የቻይና ድጋፍ እንደሚቀጥልም አስረግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በአሁኑ ወቅት ምን ይመስላል? የውዝግቡ ምክንያትስ ምን ሊሆን ይችላል? አምባሳደር ፍጹም አረጋ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር፤ ዶ/ር ወርቁ ያዕቆብ፤ በስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ ከፍተኛ ተማራማሪ  እንዲሁም የብራስልሱ ወኪላችን ጋዜጠኛ ገበያው ንጉሤ በውይይቱ ተሳታፊ ናቸው። 

ሙሉውይን ውይይት ከድምፅ ማጫወቻው ማድመጥ ይቻላል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ