1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
እምነትአፍሪቃ

ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔት እንደታገደ ነው

ማክሰኞ፣ የካቲት 7 2015

ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬም የኢንተርኔት አገልግሎት እንደተገደበ ነው። መንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ በቅርቡ ዘርፉን የተቀላቀለው የኬንያው ሳፋሪኮም የሚያቀርቡት መደበኛ የኢንተርኔት አገልግሎት አዲስ አበባን ጨምሮ እንደተገደበ ነው።

https://p.dw.com/p/4NTsm
Symbolbild Telegram Messenger blockiert
ምስል picture-alliance/dpa/TASS/A. Vaganov

ኢንተርኔት ዛሬም እንደታገደ ነው

ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬም የኢንተርኔት አገልግሎት እንደተገደበ ነው። መንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ በቅርቡ ዘርፉን የተቀላቀለው የኬንያው ሳፋሪኮም የሚያቀርቡት መደበኛ የኢንተርኔት አገልግሎት አዲስ አበባን ጨምሮ እንደተገደበ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተገልጋይ ያላቸው ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቲዩብ፤ ቲክ ቶክ እና ሜሴንጀር የተባሉ መተግበሪያዎች እየሠሩ አይደለም። በዙር አዙር ግን የኢንተርኔት አፈናውን፤ አለኢም ገደቡን የተወሰኑ ሰዎች አልፈው መጠቀም ችለዋል። በተለይ Virtual Private Network ( VPN ) እና Psiphone የተባሉ መተግበሪያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ። እነሱም ቢሆኑ ግን አገልግሎት ላይ ሲውሉ ከወትሮው በተለየ ብዙ ገንዘብ ለኢንተርኔት ያስወጣሉ።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ