ኢትዮያዊዉ ባለሐብት
ዓርብ፣ ግንቦት 22 2006ማስታወቂያ
የኢትዮጵያዊዉን ባለሐባት የአስ መሐመድን ሕይወት፤ሥራና ፈጠራን የዳሰሰ ዘጋቢ ፊልም ትንናት አዲስ አበባ ዉስጥ ተመረቀ።ከአፋር ብሔር የሚወለዱት አስ መሐመድ ከግመልና ፍየል ጠባቂነት እራሳቸዉን ለዉጠዉ ዶቢ በተባለ በረሐማ አካባቢ ጨዉ በማልማት ከፍተኛ ሐብት ለማፍራት የበቁ፤ ለበርካታ ኢትዮጵያዉያን የሥራ ዕድል የፈጠሩና ችግረኞችን የሚረዱ ባለሐብት ናቸዉ።በሸራተን አዲስ ሆቴል በተከናወነዉ የፊልም ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች አፈጉባኤዎች፤ተገኝተዉ ነበር።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ አለዉ።
ዮሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ