1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፋር 75 በመቶ ነዋሪ የምግብ እጥረት አለበት ተባለ

ሐሙስ፣ መስከረም 12 2015

75 በመቶ ያህሉ የአፋር ሕዝብን የምግብ እጥረት ያለበት ተብሎ መለየቱን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ተናገረ። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን በተለይም ለዶቼ ቬለ (DW) እንደተናገሩት ዳግም ባገረሸው ጦርነት ሰለባ የሆኑ ከ120 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው በአራት መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4HEGu
Äthiopien vom Krieg betroffene Binnenflüchtlinge aus Abala Afar-Region
ምስል Seyoum Getu/DW

75 በመቶዉ የአፋር ሕዝብን ረሐብ ያሰጋዋል

ድርቅ፣ ጦርነት እና ጎርፍ  75 በመቶ ያህሉ የአፋር ሕዝብን ለምግብ እጥረት ማጋለጡን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ተናገረ። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን በተለይም ለዶቼ ቬለ (DW) እንደተናገሩት ዳግም ባገረሸው ጦርነት ሰለባ የሆኑ ከ120 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው በአራት መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል። 

ባለፉት ሁለት ዓመታት በክልሉ በሰሜናዊ ዞን እንዲሁም በዞን አራት ውስጥ መሠረታዊ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ተቋርጠዋል ያሉት ኃላፊው ፣ የጦርነቱ መባባስ ችግሩን እንዳወሳሰበውም ገልፀዋል።

የኑሮ ውድነትን ጨምሮ በዋናነት ድርቅ፣ ቀጥሎ ጦርነት እንዲሁም ጎርፍ ከ ሁለት ሚሊዮን ያህሉ የአፋር ሕዝብ 1.4 ሚሊዮን የሚሆነው የምግብ ችግር ያለበት መሆኑን የተናገሩት የአፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን በጦርነት ምክንያት በተደጋጋሚ ተፈናቅለው መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙት ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡን አስታውቀዋል።

አክለውም "ወደ 120 ሺህ በላይ አካባቢ ሕዝብ እስካሁን ተፈናቅሎ ይገኛል። በአዲሱ ጦርነት ማለት ነው" ብለዋል። እነዚህ ሰዎች ለሦስተኛ ጊዜ የተፈናቀሉ መሆናቸውን የገለፁት አቶ መሐመድ "ከዓለም የምግብ ፕሮግራም የተለያዩ እርዳታዎች ሲቀርብላቸው ቆይቷል" በማለት እየተደረገ ስላለው ድጋፍ ገልፀዋል። 

Äthiopien vom Krieg betroffene Binnenflüchtlinge aus Abala Afar-Region
ምስል Seyoum Getu/DW

ባለፉት ሁለት ዓመታት በክልሉ በተለይ በሰሜናዊ ዞን እና በዞን አራት ውስጥ መሠረታዊ አገልግሎቶች ጦርነት እንዲቋረጡ አድርጓቸዋል ተብሏል። "ጦርነቱ እየተባባሰ ስለሆነ አንድ እንቅፋት ሆኗል" ሲሉ የክልሉ  አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ሕብረተሰቡ ለተደራራቢ ችግር መጋለጡን ተናግረዋል።

"2 ሚሊዮን ከሚገመተው የአፋር ሕዝብ ወደ 1.4 ሚሊዮን ያህሉ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ይፈልጋል" ሲሉ ዓለም ዓቀፍ ረጂ ተቋማት የበለጠ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል። 

ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ. ም ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከአፋር ክልል ለመፈናቀል የተገደዱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ከሁለት ቀናት በፊት ባወጣው ሳምንታዊ ሪፖርቱ የጠቀሰው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ በክልሉ በጎርፍ ምክንያት ብቻ 59 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ጠቅሷል። አክሎም አጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ከ16 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብሏል።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ