1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፋርማሲ ዶክተር ጠረፈወርቅ አሰግድ ሹቨ

ማክሰኞ፣ የካቲት 12 2016

ወደ ፈረንሳይ ከተመለሱ በኋላ በተመረቁበት ሞያ መሰማራት ቢፈልጉም 13 ዓመት በሙያቸው ባለመስራታቸው ሞኞታቸው ወዲያውኑ ሊሳካ አልቻለም። ግን ተስፋ ሳይቆርጡ በነጻ እያገለገሉ የስራ ልምድ አካባቱ።ያም ሆኖ በስራ ፍለጋ ወቅት ጥቁር በመሆናቸው ዘረኝነት በስራቸው ላይ ተጽእኖ ሊደርግ እንደሚችል ተነግሯቸው ነበር ። ይህ ግን አላስፈራቸውም።

https://p.dw.com/p/4cdDl
Terefwork Aseged
ምስል Hirut Melesse/DW

የፓሪስዋ ጠንካራ የፋርማሲ ዶክተር ጠረፈወርቅ አሰግድ ሹቨ

በስደት ኬንያ ከነበሩ ወላጂቻቸው ተወለዱ፣ከስደት መልስ ኢትዮጵያ አድጉ የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የዛሬ 60 ዓመት ገደማ ለከፍተኛ ትምሕርት ፈረንሳይ የመሄድ እድል አገኙ።በዶክተር ኦፍ ፋርማሲ  በተመረቁባት በፈረንሳይ አሁን በራሳቸው ፋርማሲ ውስጥ እየሰሩ ነው። ግን እዚህ ለመድረስ ውጣ ውረዶች አሳልፈዋል።  ዶክተር ጠረፈወርቅ አሰግድ ሹቨ። እንግዳችን ዶክተር ጠረፈወርቅ  ወላጆቻቸው በጣሊያን ወረራ ወቅት በተሰደዱባት በኬንያዋ ከተማ ኢሶሎ በመወለዳቸው ነው ጠረፈወርቅ የተባሉት። ኬንያ የተሰደዱት አረበኛ አባታቸው  ጣሊያን ሲሸነፍ ንጉሰ ነገስቱን አጅበው ኢትዮጵያ ሲመለሱ ጠረፈወርቅም በጨቅላ እድሜያቸው ከእናታቸው ጋር ወደ ኢትዮጵያ ሄዱ።

እድሜያቸው ለትምሕርት ሲደርስም ፊደል ቆጠሩ፣ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባው እቴጌ መነን ትምሕርት ቤት ከጀመሩ ከጥቂት ወራት በኋላ ትምሕርት በፈረንሳይኛ በሚሰጥበት ወደ ሊሴ ገብረ ማርያም ትምሕርት ቤት ገቡ ። በዚያ የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን ካጠናቀቁ በኃላ በፈረንሳይ የከፍተኛ ትምሕርት እድል አገኙ። ደቡብ ፈረንሳይ ሜዴትራንያን ባህር አቅራቢያ በምትገኘ በሞንፐልየ ከተማ ዶክተር ኦፍ ፋርማሲ እየተማሩ የአራተኛ ዓመት ተማሪ ሳሉ ከተዋወቁት ፈረንሳዊ ጋር ትዳር መሰረቱ።አንጋፋው መምህር በቦን
ጠረፈወርቅ ምኞታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ መስራት ነበርና ትምሕርታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት ከባለቤታቸው ጋር ወደ ኢትዮጵያ ቢሄዱም ባለቤታቸው የስራ ቦታ ባለማግኘታቸው ከሁለት ዓመት በኋላ እንዲጠይቁ እስከዚያም ልምድ እንዲያገኙም ወደ ኖርዊይ ሄደው እንዲሰሩ ተደረገ። በወቅቱ በርካታ ፈረንሳውያን ለነዳጅ ማውጣት ስራ ኖርዌይ ነበሩና ለልጆቻቸው በተከፈተ ትምሕርት ቤት ማስተማር ነበር ስራቸው። እርሳቸው የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ መምህር ባለቤታቸው ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ አስተማሪ ሆነው 11 ዓመት ኖርዌይ ቆዩ። በተመሳሳይ ስራ ግብጽ ሁለት ዓመት ነበሩ ። እንዳሰቡት ወደ ኢትዮጵያ ሳይሄዱ አብዮቱ ስለፈነዳ ወደ ሀገራቸው የመመለስ ተስፋቸውም ደበዘዘ

የፋርማሲ ዶክተር ጠረፈወርቅ አሰግድ
የፋርማሲ ዶክተር ጠረፈወርቅ አሰግድ ምስል Hirut Melesse/DW


 ከግብጽ ወደ ፈረንሳይ ከተመለሱ በኋላ በተመረቁበት ሞያ መሰማራት ቢፈልጉም 13 ዓመት በሙያቸው ባለመስራታቸው ሞኞታቸው ወዲያውኑ ሊሳካ አልቻለም። ኢትዮጵያዊው የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ በሐምቡርግግን ተስፋ ሳይቆርጡ በተለያዩ ፋርማሲዎች በነጻ እያገለገሉ የስራ ልምድ አካባቱ። ያም ሆኖ በስራ ፍለጋ ወቅት አሁን የራሳቸው በሆነው ፋርማሲ ውስጥ ለመቀጠር ሲመጡ እንኳን ጥቁር በመሆናቸው ዘረኝነት በስራቸው ላይ ተጽእኖ ሊደርግ እንደሚችል የፋርማሲው ባለቤት አስጠንቅቀውባቸው ነበር ። ለእርሳቸው ግን ይህ የሚያስፈራ አልነበረም። 

ዶክተር ጠረፈወርቅ በፓሪስ ወዳጆቻቸው ልደታቸውን ባከበሩበት ወቅት ደስታና ፍቅራቸውን ሲገልጹ
ዶክተር ጠረፈወርቅ በፓሪስ ወዳጆቻቸው ልደታቸውን ባከበሩበት ወቅት ደስታና ፍቅራቸውን ሲገልጹምስል Hirut Melesse/DW


ዶክተር ጠረፈወርቅ አሁን እድሜያቸው ገፍቷል ፣ ከ80 ዓመት በላይ ሆኗቸዋል። ግን ስራቸውን አላቆሙም። ለምን ሲባሉ እንዴት ያለስራ እቀመጣለሁ ነው መልሳቸው። 
ባለቤታቸው ግን ጡረታ ወጥተዋል። ከፓሪስ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ሌላ ቤታቸው ውስጥ ነው የሚኖሩት ።ግን በሳምንትም ይሁን በሁለት ሳምንት ይጠያያቃሉ ይገናኛሉ። በተለያዩ ሀገራት ተዘዋውረው የሰሩትና የኖሩት የፋርማሲ ዶክተር ጠረፈወርቅ አሰግድ ሹቨ በሄዱኩበት ሁሉ ባይተዋርነት አይሰማኝም ግን ከአገሬ አላስበልጣቸውም ይላሉ። 

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ