1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አለምአቀፉ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ቀይ መስቀል ኮሚቴ እርዳታ

ረቡዕ፣ መስከረም 25 2015

ግጭቱ ነሐሴ 24 ከቀጠለበት ዕለት ጀምሮ ግን የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት በረራ እና የተሽከርካሪ ጉዟችን ምንም እንኳን ፍላጎት ቢጨምርም ቆሟል። በሌሎች በአማራ እና በአፋር ክልሎችም አስቸካይ የህክምና ቁሳቁሶችን የማቅረብ ስራችንን ቀጥለናል"

https://p.dw.com/p/4Hn7S
Äthiopien Medizinische Hilfe des IKRK für Tigray
ምስል ICRC

የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ድጋፍ ሰቺ ኮሚቴ እርዳታ

በንፁህ ውኃ አቅርቦት፣ በመድጋኒትና የህክምና ቀሳቁስ አቅርቦት፣ ግጭትና ጦርነት ባለባቸው ቦታዎች ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ የተቋሙ የኢትዮጵያ ጽ/ቤት ቃል ዐቀባይ ጁዲ ፉንዊ  ለ DW ተናግረዋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ሦስት ክልሎች እንዲሁም በኦሮሚያ እና በሶማሊያ ክልሎችም ይሄው አስቸኳይ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።
"ከጥር 2022 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሆስፒታሎችን እና የመጀመርያ ደረጃ የጤና ተቋማት ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ ለ86 የጤና ተቋማት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገናል።
ከዚሁ ከጥር ወር ጀምሮ አለምአቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ 63 በረራዎችን እና ስምንት ተሽከርካሪዎች በጣም አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን በዋናነትም የህይወት አድን መድኃኒቶች ወደ መቀሌ አጓጉዟል።
ግጭቱ ነሐሴ 24 ከቀጠለበት ዕለት ጀምሮ ግን የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት በረራ እና የተሽከርካሪ ጉዟችን ምንም እንኳን ፍላጎት ቢጨምርም ቆሟል።
በሌሎች በአማራ እና በአፋር ክልሎችም አስቸካይ የህክምና ቁሳቁሶችን የማቅረብ ስራችንን ቀጥለናል"
ኃላፊው አክለው እንዳሉት የምግብ እና የመድኃኒት ድጋፍ ከሚሹት ዜጎች ባሻገር  የማዳበሪያና የግብርና ዘር ፣ እንዲሁም የጥሬ ገንዘብ ለሚያስፈልጋቸው የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ልዩ ልዩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
በማሳያነትም 1.6 ሚሊዮን እንስሳት እንዲከተቡ፣ 250 ሺህ አስቸኳይ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች በዚህ ማዕቀፍ እንዲጠቀሙ መደረጉንና ከ 300 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የማዳባሪያ እና የምርጥ ዘር አቅርቦት እንደታገዙም ነግረውናል።
"እነዚህን ድጋፎች የምናቀርበው ለሆስፒታሎች ነው። ስለዚህ በጦርነቱ ለቆሰሉት ሰዎች የህክምና እርዳታ ያደርጉላቸዋል ማለት ነው። የምናቀርባቸው የህክምና ቀሳቁሶች ሆስፒታሎች በጦርነቱ ለቆሰሉ ሰዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ነው"
በጦርነት ይሁን በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ተለያይተው የነበሩ ቤተሰቦችን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በስልክ በመደወል በማገናኘት መልእክት እንዲለዋወጡ አድርጌለሁ የሚለው ICRC አሁን ያለው ተጨባጭ የሀገሪቱ ሁኔታ የመፈናቀል ችግርን ማባባሱን አብራርተዋል።
"አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ  ያለው ሁኔታ የሰዎችን መፈናቀል አባብሶታል። ስለዚህ አለምአቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እያደረገ ያለው ሁኔታውን በማሰስ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በተለይ ለአዳዲስ ተፈናቃዮች የአስቸኳይ ድጋፍ ማቅረብ ነው። ብለዋል።
ሰሎሞን ሙጨ

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

እሸቴ በቀለ