1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብርቱ ዉጊያ በጎንደር

እሑድ፣ መስከረም 13 2016

በጎንደር ከተማ ከትናንት አንስቶ ብርቱ ዉጊያ እየተካሄደ መሆኑን የአይን እማኞች እና የፋኖ ቃል አቀባይ ለዶይቸ ቬለ አረጋግጠዋል።

https://p.dw.com/p/4WkgO
የጎንደር ከተማ
የጎንደር ከተማምስል Alemenew Mekonnen/DW

ጎንደር፣ ከፋኖ ቃል አቀባይ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

በጎንደር ከተማ ከትናንት ጀምሮ በመንግስት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ ሲደረግ መቆየቱን የአይን ምስክሮች ተናገሩ ። በጎንደር ከተማ በተለይ በቀበሌ 18 ሸዋ ዳቦ በሚባል አካባቢ እስከ እኩለ ቀን የደረሰ ውጊያ ሲደረግ መቆየቱን እና በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዳልቀረ እኚሁ የአይን ምስክር ተናግረዋል። የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ
« ከሌሊት አስር ሰዓት ጀምሮ በተለይ ሸዋ ዳቦ 18 በሚባል እኔ ባለሁበት አካባቢ በፋኖ እና በመከላከያ 10 ሰዓት ነው የጀመረው ። ጥዋት ስነሳ ውጊያ ነው ፤ ወደ ውጭ መውጣትም አልተቻለም ። ለአንድ አፍታ ስንወጣ የወደቀም አለ ፤ አንድ የመከላከያ መኪናም የተቃጠለ አለ ። ከዚያ ውጭ የፋኖ ታጣቂዎች ቀበሌ 18 አብዛኛ አካባቢ አሉ። መከላከያም በዙሪያው አለ፤ ተኩሱም እንዳለ ነው። » በከተማ የእንቅስቃሴ መስተጓጎል እንዳለ የነገሩን እኙሁ የከተማዋ ነዋሪ  ውጥረቱ አይሎ መቀጠሉን ገልጸዋል።
« 18 አሁንም ውጥረት ነው ተኩስ አለ ፤ አልፎ አልፎ የከባድ መሳሪያ ድምጽ ይሰማል። ህዝቡም ያው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴም የለም ፤ ቁጭ ብሎ ማየት ነው።»
በጎንደር ከተማ ከትናንት አንስቶ ብርቱ ዉጊያ እየተካሄደ መሆኑን  የአይን እማኞች ብቻ ሳይሆኑ የፋኖ ቃል አቀባይም ለዶይቸ ቬለ አረጋግጠዋል።  ለደህንነታቸው ሲባል በስም መጠቀስ የማይፈልጉት እና ራሳቸውን የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ ቃል አቀባይ ብለው የሚጠሩት ግለሰብ እንደገለፁልን ትናንትና አመሻሽ ጀምሮ «የሁለተኛው የትግሉ ምልዕፍ የመጀመሪያ ዙር የማጥቃት እንቅስቃሴ ተጀምሯል» ብለዋል። ቃለ መጠይቁ ከዘገባው ጋር ተያይዟል። የአማራ ክልል ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና ኮማንድ ፖስት

በጎንደር ከተማ የአጼ ቴዎድሮስ ሀውልት የሚገኝበት የፒያሳ አደባባይ
በጎንደር ከተማ ከትናንት አንስቶ ብርቱ ዉጊያ እየተካሄደ መሆኑን  የአይን እማኞች ብቻ ሳይሆኑ የፋኖ ቃል አቀባይም ለዶይቸ ቬለ አረጋግጠዋል።  ለደህንነታቸው ሲባል በስም መጠቀስ የማይፈልጉት እና ራሳቸውን የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ ቃል አቀባይ ብለው የሚጠሩት ግለሰብ እንደገለፁልን ትናንትና አመሻሽ ጀምሮ «የሁለተኛው የትግሉ ምልዕፍ የመጀመሪያ ዙር የማጥቃት እንቅስቃሴ ተጀምሯል» ብለዋል። ምስል Nebiyu Sirak/DW

በከተማዋ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በመንግሥት በኩል ለማረጋገጥ ከከተማዋ እና ከክልሉ ባለስልጣናት ለማረጋገጥ ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ስልክ ባለመነሳቱ ሳይሳካ ቀርቷል። የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ  ወደሆኑት ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ለመደወል ያደረግነው ጥረትም  ስልክ ባለመስራቱ እንዲሁ ሳይሳካ ቀርቷል። 

ልደት አበበ

ታምራት ዲንሳ