1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሪታንያ፤ ህገወጥ የተባሉትን ስደተኞችን ወደ ርዋንዳ የመመለስ እቅድ ተሰርዟል መባሉ

ዓርብ፣ ሐምሌ 5 2016

የሐምሌ አምስቱን የብሪታንያ ምርጫና የሠራተኛው ፓርቲ ጠቅላላ ድልን ተከትሎ አዲሱ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪየር ስታርመር የመጀመርያ የቢሮ ስራቸው ባለፈው በወግ አጥባቂው ፓርቲ ተደንግጎ የነበረውን ህገወጥ የተባሉትን ስደተኞችን ወደ ርዋንዳ የመመለስ ስራ ከመሰረቱ መሰረዝ መሆኑን አስታውቀዋል። “ዋናው መርሀችን ህዝብን ማገልገል ነው”

https://p.dw.com/p/4iE9m
ፎቶ ማህደር፤ ስደተኞች ይጠረዙ የሚለዉን የተቃወሙ ሰልፈኞች በለንደን
ፎቶ ማህደር፤ ስደተኞች ይጠረዙ የሚለዉን የተቃወሙ ሰልፈኞች በለንደን ምስል Niklas Halle'n/AFP/ Getty Images

ብሪታንያ፤ ህገወጥ የተባሉትን ስደተኞችን ወደ ርዋንዳ የመመለስ እቅድ ይሰረዛል መባሉ


የሐምሌ አምስቱን የብሪታንያ ምርጫና የሠራተኛው ፓርቲ ጠቅላላ ድልን ተከትሎ አዲሱ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪየር ስታርመር የመጀመርያ የቢሮ ስራቸው ባለፈው በወግ አጥባቂው ፓርቲ ተደንግጎ የነበረውን ህገወጥ የተባሉትን ስደተኞችን ወደ ርዋንዳ የመመለስ ስራ ከመሰረቱ መሰረዝ መሆኑን አስታውቀዋል።  “ዋናው መርሀችን ህዝብን ማገልገል ነው ፣ የመረጠንንም ሆነ ያልመረጠንን የብሪታንያ ህዝብ እኩል እናገለግላለን፣ አመሰግናለሁ”
የብሪታንያ ታክስ ከፋይ በብዙ ሚሊዮኖች ፐውን ድ የሚቆጠር ገንዘብ እቅዱን ለማስፈፀም በአንድ ስደተኛ ላይ እንኳ ተግባራዊ ሳይሆን መፍረሱ የወግ አጥባቂው ፓርቲ ሪሺ ሱናክ መንግስት መሳለቂያ አድርጎታል። ይህ ውል መጀመርያየተፈረመው በቀድሞው በዚሁ የወግ አጥባቂው ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት ቦሪስ ጆንሰን ሲሆንከርሳቸው በውሀላ የመጡት ሱናክ በሀምሌ 24 , 2024 ከምርጫው ድል በውሀላ የመጀመርያው ተመላሽ የስደተኛ ቡድን ወደ ርዋንዳ እንደሚላክ እንዳስገነዘቡ ይታወሳል።
ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ውሳኔ አዲሷ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ይቬት ኩፐር የወግ አጥባቂው ፓርቲ መንግስት ያዘጋጀውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ኦዲት ካደረጉ በውሀላወደ ድንበር ጥበቃና ስደተኞች በህገወጥ መንገድ እንዳይገቡ የድንበር ፖሊስ ወደ ማሰልጠን እንደሚመድቡት አስታውቀዋል።

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ይህ ያለአግባብ ከብሪታንያ ታክስ ከፋይ የተሰበሰበው ገንዘብ ወደ ሌላ ቦታ እንዲመደብ አስተካክለናል” ይህንኑ ተከትሎ በለንደን እና አካባቢው የመኖሩ የስደተኞች ድርጅቶች የፕሮግራሙን መሰረዝ እየደገፉ ይገኛሉ፣“ብዙም የፓለቲካ እውቀት የለኝም ነገር ግን ይህ ነገር ለብዙስደተኛ እዚህ አገር ለሚኖረው ስደተኛ ጥሩ ዜና እንደሆነ ግን እገምታለሁ” “ በስንት መከራ እዚህ ደርሰን ወደርዋንዳ መመለስ ልክ አልነበረም ከመጀመርያው አሁን በውሳኔው ተደስተናል” ይህ ከግማሽ በሊዮን ፓውንድ በላይ የወሰደ ፕሮጀክት በኪሳራ ወጭነት ተመዝግቦ ተሰርዟል።

መኮንን ሚካኤል
አዜብ ታደሰ 
ፀሐይ ጫኔ