1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሕአዴግ ዉሕደትና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

ማክሰኞ፣ ኅዳር 23 2012

የአማራ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር የሕግ አማካሪ አቶ መረሐፅድቅ መኮንን የአቶ ለማ አስተያየት የኢሕአዴግን የመዋሐድ ሒደት አያዉክም ባይ ናቸዉ።ሌሎች የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሥለሚመሰረተዉ የብልፅግና ፓርቲ ድጋፍም ተቃዉሞም አላቸዉ።የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም በብልፅግና ፓርቲ አመሠራረት፣ዓላማና ምግባር ላይ ሶስት ተቃራኒ አስተያዬቶችን እየሰነዘሩ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3UA0h
Merhatsiedk Mekonnen Amhara Region
ምስል DW/A. Mekonnen

 ብልፅግና ፓርቲ፣የለማ ተቃዉሞና አፀፋዉ

ባለፈዉ ሳምንት ራሱን ያከሰመዉ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ምክትል ሊቀመንበርና የመከላከያ ሚንስትር ለማ መገርሳ ባለፈዉ ሳምንት የኢሕአዴግን መዋሐድ በመቃወም የሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያዉያንን እያነጋገረ ነዉ።የአማራ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር የሕግ አማካሪ አቶ መረሐፅድቅ መኮንን ግን የአቶ ለማ አስተያየት የኢሕአዴግን የመዋሐድ ሒደት አያዉክም ባይ ናቸዉ።ሌሎች የአማራ ክልል ነዋሪዎች አዲስ ሥለሚመሰረተዉ የብልፅግና ፓርቲ ድጋፍም ተቃዉሞም አላቸዉ።ዓለምነዉ መኮንን አስተያዬቶችን ሰብስቧል።የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም አዲስ በሚመሰረተዉ የብልፅግና ፓርቲ አመሠራረት፣ዓላማና ምግባር ላይ ሶስት ተቃራኒ አስተያዬቶችን እየሰነዘሩ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን  ካነጋገራቸዉ የከተማይቱ ነዋሪዎች ገሚሱ የብልፅግና ፓርቲ መመስረቱን ሲደግፉ ሌሎች ኢሕአዴግ ተሻሽሎ እንደነበረ መቀጠል ነበረበት ባዮች ናቸዉ።ከሁለቱ ለየት ያለ አስተያየት የሚሰጡት ደግሞ የኢሕአዴግን መዋሐድ ቢደግፉም ዉሕደቱ በጣም ፈጠነ ይላሉ። ዝርዝሩን እነሆ።

አለምነው መኮንን

ሰሎሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ 

ኂሩት መለሰ


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ