1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባለፈው አንድ ዓመት ከዚህ በፊት ያልታዩ የመብት ጥሰቶች ታይተዋል፤ ኢሰመኮ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 5 2015

ኮሚሽኑ ከሰኔ 2014 እስከ ሰኔ 2015 ዓ. ም ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ በዳሰሰበት ዘገባው "በሀገሪቱ ከዚህ በፊት ያልታዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተስተውለዋል፣ መጠናቸው እና አሳሳቢነታቸውም ሰፍቷል" ይላል። የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተለይ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ጎልቶ መስተዋሉንም የኮሚሽኑ ሪፓርት ያሳያል

https://p.dw.com/p/4TmPQ
Äthiopien Menschenrechtskommission
ምስል Solomon Muche/DW

በሰብዓዊ መብት አያያዝ ረገድ ወደኋላ የመንሸራተት ሥጋት እና አዝማሚያ ታይቷል

ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፈው አንድ ዓመት "በሰብዓዊ መብት አያያዝ ረገድ ወደኋላ የመንሸራተት ሥጋት እና አዝማሚያ ታይቷል" ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያደረገው የዓንድ አመት የመብት ምርመራ የተጠቃለለ ዘገባ አመልከተ። 

ኮሚሽኑ ከሰኔ 2014 እስከ ሰኔ 2015 ዓ. ም ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ በዳሰሰበት ዘገባው "በሀገሪቱ ከዚህ በፊት ያልታዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተስተውለዋል፣ መጠናቸው እና አሳሳቢነታቸውም ሰፍቷል" ይላል። የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተለይ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ጎልቶ መስተዋሉንም የኮሚሽኑ ሪፓርት ያሳያል። 

ኢሰመኮ በሁሉም ክልሎች እሁንም በአሳሳቢነታቸው የቀጠሉ ያላቸው ጥሰቶች መቀጠላቸውን ፣ የታጠቁ ቡድኖች ጥቃቶች እና ግጭቶች አሁንም ዘላቂ ፖለቲካዊ እና መዋቅራዊ መፍፍትሔ ያልተሰጣቸው መሆኑ በሰዎች የመኖር መብት አያያዝ ላይ ትርጉም ያለው መሻሻል እንዳይኖር አድርጓል ሲል አስታውቋል። በዚህ ችግር ምክንያት በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች የሰዎች እንቅስቃሴ መገደቡን ፣ ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ እንደወደቀ መቀጠሉንም ይፋ አድርጓል።በሸገር ከተማ ቤቶች መፍረስ እና የኢሰመኮ መግለጫ
ቀጥሏላ።
ኢሰመኮ የአሜሪካ መንግሥት በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ስልታዊ ባህሪ ያላቸው መሆኑ ላይ ከዚህ በፊት ይዞት ከነበረው አቋም የተለየ ድምዳሜ ላይ መድረሱን እና አቋሙን መቀየሩን ያስታወቀበት አቋም ኮሚሽኑ ካወጣው ዘገባ ጋር የማይጋጭ መሆኑን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ከ ዶቼ ቬለ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አረጋግጠዋል። 

Äthiopien Menschenrechtskommission
ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለምስል Solomon Muche/DW

ኢሰመኮ "ካለፈው ዓመት አንጻር ግጭቶችን በሰላም በመፍታት ረገድ አበረታች" ያላቸው ጅማሮዎች መኖራቸውንም ዘገባውን ዛሬ ይፋ ሲያደርግ አስታውቋል።

ኢሰመኮ በአመቱ ያደረገው ምርመራ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዋነኛ ምክንያት ያላቸው የተጠያቂነት አለመኖር፣ የሕግ የበላይነት መላላት እና የሰላም እና ደኅንነት እጦትን በተመለከተ ዘላቂ መፍትሔ በመስጠት ረገድ የመንግሥት ከፍተኛ እና ያልተቋረጠ ጥረት አለመኖር መሆናቸውን ዛሬ በኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በተሰጠው መግለጫ ተዘርዝሯል። የኢሰመኮ እና የአፋር ተፈናቃዮች ስጋት
የትጥቅ ግጭቶችን በሰላም በመፍታት ረገድ አበረታች ጅማሮች መኖራቸውን ያስታወሰው ኮሚሽኑ፣ ዘላቂ እና በሀገራዊው የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ተጨባጭ መሻሻል እንዲያመጡ የሰላም ጥረቶች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ተጎጂ ማኅበረሰቦችን በማሳተፍ ረገድ አካታች ሊሆኑ እንደሚገባ በሪፖርቱ አሳስቧል። 
"በሚዲያ፣ በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ በማኅበረሰብ አንቂዎች እና ሲቪክ ማኅበረሰብ አባላት ላይ ያነጣጠሩ ወከባ እና እስሮች፣ የጸጥታ ችግሮችን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶችና አካባቢዎች ጊዜያዊም ሆነ ረዘም ያለ ጊዜ የቆዩ የመንቀሳቀስ ገደቦች በእራሳቸው የመብት ጥሰቶች ከመሆናቸውም በተጨማሪ፣ በሰዎች ላይ እያደረሱ ያሉት ሥጋት፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ቀውሶች ሀገራዊውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አሳሳቢ ካደረጉ ሁኔታዎች መካከል ናቸው" ሲል ዋና ኮሚሽነር ዴክተር ዳንኤል በቀለ ያቀረቡት የኮሚሽኑ የምርመራ ውጤት ያሳያል። 

Äthiopien Menschenrechtskommission
የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኃላፊዎች ከመግለጫው በኋላምስል Solomon Muche/DW

ዓመታዊው የምርመራ ዘገባ ካለፈው ዓመት አንጻር ግጭቶችን በሰላም በመፍታት ረገድ አበረታች ጅማሮዎች ቢስተዋሉም፣ ተለዋዋጭ እና ዘርፈ ብዙ የመብቶች ጥሰቶች በተለያዩ የመንግሥት መዋቅሮች እና መንግሥታዊ ባልሆኑ አካላት መፈጸማቸውን አብራርቷል። ስለ ኦሮሚያ ክልል የሰብዓዊ ቀውሶች የኢሰመኮ መግለጫ
ክልሎች መካከል እና በአንድ ክልል ውስጥ ያሉ አስተዳደራዊ፣ የመዋቅር እና የድንበር መካለል ጥያቄዎች ለተጨማሪ ግጭት እና የሕይወት መጥፋት ምክንያት እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥረት ሊደረግ ይገባል ያለው ኢሰመኮ በዓመቱ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ረገድ ወደኋላ የመንሸራተት ሥጋት እና አዝማሚያ ታይቷል" ሲል አስታውቋል።

ዋና ኮሚሽነሩ የአሜሪካ መንግሥት በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ስልታዊነት ላይ ከዚህ በፊት ይዞት ከነበረው አቋም የተለየ ድምዳሜ ላይ መድረሱን በተመለከተ ተጠይቀው አቋሙ ኮሚሽኑ ካወጣው የዚህ ዓመት ዘገባ ጋር የማይጋጭ ነው ብለዋል።የኢሰመኮ ዓመታዊ መግለጫ
የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ፣ ተጎጅዎችን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን የዘፈቀደ እሥር ፣ በውል የማይታወቁ የማቆያ ሥፍራዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣት ፣ በጎዳና ላይ ያሉ ሕፃናትን በጅምላ ማፈስ እንዲቆምና ኢንተርኔት ላይ የተጣለው ገደብ እንዲነሳ ተጠይቋል።
የተቋሙን ገለልተኝነት በተመለከተ ለቀረበ ጥያቄም ኮሚሽኑ "ሙሉ በሙሉ ገለልተኛ ተቋም ነው" የሚል ምላሽ ተሰጥቷል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ