1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባህር ዳር ሟቾችን ስትቀብር ዋለች

ሐሙስ፣ ነሐሴ 4 2015

በውጊያው የሞቱ ሰዎች ስርዓተ ቀብር ዛሬ በተለያየ ቦታ መፈጸሙን የባህር ዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን ዘግቧል። ከሟቾቹ አብዛኛዎቹ ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ናቸው ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ከባህር ዳር ማረሚያ ቤት ብቻ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ያሏቸው ታራሚዎች ሲወጡ ማየታቸውንም ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/4Uxip
Äthiopien Bahirdar Covid19
የባህርዳር ከተማ አንዱ ክፍልምስል DW/A. Mekonnen

 

ባህር ዳር በትናንቱ ውጊያ የሞቱባትን ነዋሪዎችዋን ዛሬ ስትቀብር ውላለች። ትናንት በባህርዳር ከተማ በተለይ በሦስት ቀበሌዎች በፋኖና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በተካሄደ ውጊያ በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን በሟቾች ቀብር ላይ የተገኙ አስተያየት ሰጭዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል። በውጊያው የሞቱ ሰዎች ስርዓተ ቀብር ዛሬ በተለያየ ቦታ መፈጸሙን የባህርዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን ዘግቧል። ከሞቾቹ አብዛኛዎቹ ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ናቸው ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ከባህር ዳር ማረሚያ ቤት ብቻ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ያሏቸው ታራሚዎች ሲወጡ ማየታቸውንም ተናግረዋል። ባህር ዳር ከትናንት ከሰዓት አንስቶ እስከ ዛሬ ምሽት ድረስ ተኩስ እንዳልተሰማባት አለምነው ዘግቧል።

 

አለምነው መኮንን

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ