1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባህላዊው ሽምግልና እና የፖለቲካው ተፅዕኖ

እሑድ፣ ታኅሣሥ 13 2017

በግለሰብም ሆነ በማኅበረሰብ መካከል ግጭት ፀብን ለማርገብ፣ ብሎም ሰላምን ለማስፈን ሽምግልና ኢትዮጵያ ውስጥ በየማኅበረሰቡ የረዥም ዘመናት ማኅበራዊ እሴት ሆኖ ቆይቷል። በአሁኑ ጊዜ ግን በአመዛኙ ይህ ማኅበራዊ እሴት የቀድሞ ክብሩን እያጣ፣ ወግ ያለው የማረጋጋት ሚናውም እየደበዘዘ መምጣቱን ብዙዎች በማንሳት ይተቻሉ።

https://p.dw.com/p/4oQkO
የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች
የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች የተሰባሰቡበት ሸንጎ ፎቶ ከማኅደር ምስል privat

ባህላዊው ሽምግልና እና የፖለቲካው ተፅዕኖ

ሽምግልና ኢትዮጵያ ውስጥ ለረዥም ዘመናት የቆየ ማኅበራዊ እሴት በመሆን ይታወቃል። ባህላዊው የሽምግልና ሂደት በግለሰቦች መካከል የሚነሳ አለመግባባትን ከመፍታት አንስቶ እስከ ማኅበረሰብ ብሎም በሀገራዊ ደረጃም ለሚፈጠሩ ችግሮች ጉልህ ሚና ሲጫወት ኖሯል። በየማኅበረሰቡም ለሽምግልና እና ሸምጋዮች ኅብተሰቡ ከፍተኛ ክብር ይሰጣል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ይህ የተከበረ ማኅበራዊ እሴት የቀድሞ ደረጃውን እንዲያጣ፤ ተዓማኒነትም እንዳይኖረው የሚያደርጉ አካሄዶች እየታዩ በመሆኑ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬም ባላደገው ፖለቲካና የተሳዛቡ ትርክቶች ያስከተሉት ማኅበራዊ ውጥንቅጥ የብዙሃኑን ምስኪን ሕዝብ ኑሮ እያወከ መፍትሄ ማምጣት አለመቻሉ ይታያል። ለዚህ ደግሞ የፖለቲካውን ጣልቃ ገብነት ተጠያቂ የሚያደርጉ ጥቂት አይደሉም።

ዶቼ ቬለ በባህላዊው ሽምግልና ሂደት የፖለቲካው ተፅዕኖ፣ በሚል ርዕስ ባካሄደው ውይይት ሦስት ተሳትፈው ሃሳብ አስተያየታቸውን አጋርተዋል። ፕሮፌሰር ቢንያም አዋሽ በኒዉዮርክ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ መምህር፤ አቶ ዳዊት ሳሙኤል የማኅበራዊ ስነሰብ ምሁር እንዲሁም መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ /ኢሕአፓ/ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ናቸው ተወያዮቹ። 

ሙሉውን ውይይት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ