1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቡና በዓለም ገበያ

ረቡዕ፣ የካቲት 10 2013

የቡና አምራች ሃገራት ገበሬዎች ያመረቱትን ቡና ቆልተውና ፈጭተው በማሸግ ለገበያ ከሚያቀርቡት ኩባንያዎች እጅግ ያነሰ ገቢ እንደሚያገኙ በየጊዜው ይነገራል። በተለይም በአውሮጳና በሰሜን አሜሪካ የቡና ገበያውን ለተመለከተ በሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር እንደሚዛቅበት ያስተውላል።

https://p.dw.com/p/3pUDh
Kafeeernte in Äthiopien
ምስል Reuters/M. Haileselassie

አምራቹ ብዙም የማያገኝበት ቡና

የተጠቃሚው ቁጥር እዚህ ጨምሮ የቡና ዋጋ በየጊዜው ወደላይ እየመጠቀ ነው። ግንቡ ፈርሶ የምሥራቅ አውሮጳና የእስያ ነዋሪዎች ቡና ጠጪ ከሆኑ ወዲህ ደግሞ ገበያው ደርቷል። በተቃራኒው አምራቹ ገበሬ ከቡና ለቃሚው ጋር ከቡና ሽያጭ የሚያገኘው ገንዘብ ወደታች በየጊዜው እያሽቆለቆለ ይገኛል። የቡና አምራች ሃገራት ገበሬዎች ያመረቱትን ቡና ቆልተውና ፈጭተው በማሸግ ለገበያ ከሚያቀርቡት ኩባንያዎች እጅግ ያነሰ ገቢ እንደሚያገኙ በየጊዜው ይነገራል። በተለይም በአውሮጳና በሰሜን አሜሪካ የቡና ገበያውን ለተመለከተ በሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር እንደሚዛቅበት ያስተውላል።

 ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ