1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጎረቤት አገሮች የሚካሄዱ ግጭቶች በኢትዮጵያ ላይ የጋረጡት ፈተና

ዓርብ፣ መስከረም 24 2017

«ጎረቤት ኤርትራ ሱዳን ሱማሊያ ጅቡቲ አንድም በውስጥ አለያም በውጭ ጉዳዮች ሆድ እየባሳቸው ተቸግረዋል።ይህም በዚህም በዚያም ብቅ ጥልቅ በሚሉ ግጭቶች እየተተራመሰች ከተማዋን በማደስ ስራ ተጠምጃለሁ ለምትለው ኢትዪጵያ ያለባትን ፈተና አጠንክሮታል። ኢትዮጵያ ለምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት የምታደርገውን ጥረት ለራስዋ ስትል መቀጠል አለባት።»

https://p.dw.com/p/4lQpV
Äthiopien Botschafter Taye Atske Silassie
ምስል Solomon Muchie/DW

በጎረቤት አገሮች የሚካሄዱ ግጭቶች በኢትዮጵያ ላይ ያሳደሩት ተጽእኖ

የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) የቡርኪና ፋሶ፣ የማሊና የኒጀር ወታደራዊ መሪዎች፣ በኮንፌዴሬሽን ለመዋሃድ መስማማታቸው ሲሰማ እንዴት ተደርጎ በሚል ሀገር ይያያዝ እያሉ ነው ፡፡ የመካከለኛው እና ምስራቅና አፍሪካ ህዝቦችምሰላም ጠምቷቸዋል።

« እዚህ በጎረቤት ኤርትራ ሱዳን ሱማሊያ ጅቡቲ አንድም በውስጥ አንድም በውጭ ሆድ እየባሳቸው ተቸግረዋል ይሄ ደግሞ  «በዚህም በዚያም ብቅ ጥልቅ በሚሉ ግጭቶች እየተተራመሰች ዋና ከተማዋን በማደስ ስራ ላይ ተጠምጃለሁ ለምትለው ኢትዪጵያ ያለባትን ፈተና አጠንክሮታል። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ በተለይም ለምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት የምታደርገውን ጥረት ለራስዋ ስትል መቀጠል አለባት ፣በተለይ ለረጅም ዘመናት በውስጥ ጉዳይዋ ጣልቃ እየገቡ እራስ ምታት ሆነውባት የነበሩት ሀገራት በግጭት ተከበው እና ታምሰው ባሉበት በዚህ ወቅት የራስዋን የቤት ሰራ አለመስርትዋ አጋጣሚውን እንዳትጠቀምበት ምክንያት ሆንዋል ፤ሲሉ ለ DW የተናገሩት  በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና አለማቀፍ ትምህርት ክፍል መምህር አቶ እያሱ ግዛው ናቸው

የሀርጌሳ ከተማ
የሀርጌሳ ከተማምስል Eshete Bekele/DW

በምስራቅ አፍሪካ እና በ አፍሪካ ቀንድ  የሚኖረው ማነኛውም አለመረጋጋት ለአትዮጵያ መህኅበራዊ ኢኮኒሚያዊ እና ፓለቲካዊ እንቅፋት ነው ያሉት የፓለቲካ እና የአለማቀፍ ትምህርት መምህር ኢትዮጵያ አጥብቃ መስራት ያለባት ቤትዋ ሰላም እንዲሆን ለጎረቤቶችዋ ስላም ማደር ነው ብለዋል አቶ እያሱ ።ከዚህ ሌላ አቶ እያሱ በተለይ የምስራቅ አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ጦርነት ያለበት አካባቢ ነው። እንደተፈጥሮ ፍቃድ ሆኖ በአካባቤው እጅግ ወሳኝ የሆነ መልከአምድር ይዛ የምትገኛው ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምስራቅ የሚካሄደውን ግጭት በተመለከተ የራስዋን ጥቅም ሊያስጠብቅ በሚችል መልኩ ለመወሰን የሚያስችላትን ስራ መስራት አለባት ብለዋል።

 

ሀና ደምሴ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ